ሰላም ሰዎች መፅሀፍ ቅዱስ ላይ የስላሴ ስም ውስን ቦታ ነው የተጠቀሰው አይደል እስቲ የተጠቀሰበትን ቦታ ጠቁሙኝ
Jun 12, 2021በመጀመሪያ ሥላሴ ማለት ሠለሰ ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን ሦስትነት ማለት ነው፣ ቃሉም የግእዝ ነው። ይህ ቃል የአምላክ ን አንድነትና ሦስትነትን ያመለክታል። ትምህርተ ሥላሴ እንደሚለን፣ እግዚአብሔር ፈጣሪ አንድላይ በሦስት ቦታዎች ሊኖር ይችላል። ፩) በ መሢሕ ይኖራል ( ወልድ )፤ ፪) በልባችን ይኖራል (መንፈስ ቅዱስ )፤ ፫) በማይታይ ሰማያት የትም ቦታ ይኖራል ( አብ )። ይሁን እንጂ ሦስቱም አንድ አምላክ ናቸው እንጂ ሦስት አማልክት አይደሉም። ስለዚህ ቀኖና የተሰጡ ሌሎች መግለጫዎች እንደሚያመለክቱት እነዚህ ሦስት "አካላት" መለኮታዊው ህልውና የሚገለጥባቸው ሦስት መንገዶች ናቸው እንጂ የተለያዩና ግላዊ ሕልውና ያላቸው "አካላት" አይደሉም። በዚህም ምክንያት አንዳንድ የሥላሴ አማኞች ኢየሱስ እግዚአብሔር እንደሆነ ወይም ኢየሱስና መንፈስ ቅዱስ ይሖዋ እንደሆኑ አጥብቀው ያምናሉ። አምላክ አንድ ሲሆን ሶስት ሶስት ሲሆን አንድ ማለት ነው፤ በስም፣ በአካል እና በግብር ሶስት ሲሆን በህላዌ እና በመለኮት አንድ ነው። 🏳ክርስቶስ ከመወለዱ በፊት የሥላሴ ሦሥትነትና አንድነት በብሉይ ኪዳን ብዙ ቦታ ተጽፎ ይገኛል። ነገር ግን በዛን ወቅት የነበሩ ነብያትም ሆኑ አስተማሪዎች ነገሩ አልተገለፀላቸውም ነበር። በግልፅ በመጻሕፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚነበቡት፦ 👉አዳም ን በአምሳላችን እንፍጠር ፣ 👉አዳም እንደኛ አንዱ ሆነ ፣ 👉የሰናዖር ን ሰዎች ቋንቋ በመለያየታቸው ፣ 👉በ አብርሃም ቤት በመስተናገዳቸው 👉ዳዊት በመዝሙር "ጌታ ጌታዬን ጠላትህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ በቀኜ ተቀመጥ" ብሎ በጻፈው… 🏳ክርስቶስ ከመጣ በኋላ ግን የተሸፈነው ሁሉ ተገልጾ በተግባር አንድም ሦሥትም መሆናቸውን ኢየሱስ አሳወቀም አስተማረም 🎯እየሩሳሌም በበዐል ቀን ጠፍቶ ሲገኝ ለእናቱ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ና ለ ቅዱስ ዮሴፍ ሲመልስ "በአባቴ ቤት መኖር እንዳለብኝ አታውቁምን" በማለቱ፣ 🎯በዮርዳኖስ ጥምቀቱ ''መንፈስ ቅዱስ በነጭ እርግብ ተመስሎ በላዩላይ በመቀመጡ ፣ የእግዚአብሔርም አብ ቃል "ይህ የምወደው የምወልደው ልጄ ነው እሱ የሚላችሁን በሙሉ ስሙት" ባለው፣ 🎯በ ደብረ ታቦር የጌትነቱ ግርማ ማለትም መላ ሰውነቱና ልብሱ በሚያስደንቅ ብርሃን በመሞላቱ ፣ 🎯ለፍሊጶስ እኔን ካያቹህ አብን አባቴን እንዳያቹህ ቁጠሩ፣ 🎯አባታችን ሆይ ጸሎት በማስተማሩ… 🏳ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ከዐረገ በኋላም፦ 🎯 በ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማዕትነት ጊዜ በ ሐዋ.ሥ. -ም፡፯ ቁ፡፶፭-፶፮ ላይ እንደተጻፈው መንፈስ፡ቅዱስንም፡ተሞልቶ፡ወደ፡ሰማይ፡ትኵር፡ብሎ፡ሲመለከት፡ የእግዚአብሔርን፡ክብር፡ኢየሱስንም በእግዚአብሔር፡ቀኝ፡ቆሞ፡አየና፦ እንሆ፥ሰማያት፡ተከፍተው፡የሰው፡ልጅም፡በ እግዚአብሔር ፡ቀኝ፡ቆሞ፡ አያለኹ፡አለ። lebelete memeher teyeki enji termu ke egna nw😉
Jun 13, 2021