ከመስቀል አደባባይ እና እስከ ማዘጋጃ ቤት ፕሮጀክት የምረቃ ስነስርዓት ስለሚካሄድ ነገ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በመሆኑም የምረቃ እና ስርዓቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን የላይኛው አደባባይ ፒያሳ ጣሊያን ሰፈር መግቢያ ሱማሌ ተራ አካባቢ የሚገኘው አደባባይ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ ጎላ ሚካኤል ጥቁር አንበሳ ሼል ሜትሮሎጂ ጎማ ቁጠባ ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ ለገሃር ጉምሩክ መብራት ቡናና ሻይ ገነት መብራት 4ኛ ክፍለ ጦር (ጥላሁን አደባባይ) ቂርቆስ መታጠፊያ አጎና ሲኒማ ኦሎምፒያ ኡራኤል አደባባይ ባምቢስ መታጠፊያ ካዛንቺስ ሼል ፍልውሃ ሸራተን አካባቢ መስጊድ ኦርማ ጋራዥ ንግድ ማተሚ ቤት ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆን አሽከርካሪዎች ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና የጋራ ለሆነው ሰላማችን አስፈላጊውን ትብብር እንዲደርጉ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
Jun 12, 2021