ታቃላችሁ በጣም ይከፍኛል ቤተሰቦቼ ምንም ሳላደርግ ሳላፍ የሚናገሩኝ ነገር እኔ ኮ ብታዩኝ እውነት አሁን 19 አመቴን ልይዝ ነኝ ከቤት ኮሌጅ ከኮሌጅ ክላስ እየመጣሁ እ ትምህርት ቤትም እንደዛው ነበር አሁንም እንደዛው ነኝ በቃ ቆንጆ ነኝ የእውነት በቃ ፈጣሪ እንደፈጠርኝ ቤት እንኳን ከገባው ክላስ ከሌሌ የትም አልሄድም ብታምኑም ባታምኑም ልደትም ሆነ ሰርግ ሂጄም ተከብሮልኝም አያውቅም ኑሮ ግን ሰልችቶኛል የሆነ ባህሪሽ ተቀየር ሰከን በይ ይሉኛል ስልክ እንኳን ስጠቀም አይጠቅምሽም ብለው በሱ ደሞ ይቆጡኛል ቤት ውስጥ እንኳን ስራ በደምብ ነው የምሰራው እወዳቸዋለው ግን የዚ ዘመን እንኳን የማልመስለውን ለምን እንደማይንከባከቡኝ ነው የሚገርመኝ እኔ ፍቅራቸውን ካላሳዩኝ ምንም ህይወት እንደሌለኝ ማወቅ ነበርባቸው አይመስላችሁም
Jun 11, 2021የአብዛኛው የሀበሻ ወላጅ ችግር ነው ልጅን በስርዐት ማሳደግ ላይ ጥሩ ሆነው ግን ለእሱ በህይወት አስፈላጊ ነገር መብላት መጠጣት በቃ መማር ነው ይሄ ብዙ ሰው ጋር አለ አንቺም ታጋሽ ለመሆን ሞክሩ የእድሜ ጉዳይ ነው ከትንሽ ጊዜ በኀላ ሊቆጣጠሩሽ እንደማይችሉ ይገባቸዋል
Jun 12, 2021