ye 12tgna kefel social science temari neg Ena mnm makew nger ylm le entrance i am so stressed Theory mibzabachwen tmertoch Be achir menged le entrance mzgajibetn mnged pls tell me Ena my last question ye natural ena social Common tmertoch ytelyaye fetna ymiweta ymslachwal
Jun 09, 2021ወዳጄ እኔም እንዳንተው የ 12ኛ ክፍል የማኅበራዊ ሳይንስ (ሶሻል) ተማሪ ነኝ። ከሁሉም በፊት መጨናነቅህን አቁም። አጠናህም አላጠናህም ፈጣሪህ ከወሰነልህ ውጭ የምታመጣው ነገር እንደሌለ እመንና መጨናነቅን መፍትሄ አታድርግ ሀቢቢ። በተረፈ የለፋኸውን ፈጣሪህ እንደሚሰጥህ አምነህ ተቀበል። ወደ መፍትሄው ልውሰድህ.. ንባብ መጀመር የነበረብህ ቀደም ብለህ የነበረ ቢሆንም አሁንም አልረፈደም። ዛሬ አሁኑኑ ጀምር። እኔ የማደርገውን ልንገርህ.. እንደኔ ምንም ስራ (ራስን ማስተዳደርም ሆነ ቤተሰብ ማገዝ) ከሌለህ እንደኔ አድርግ። መጀመሪያ የሁለቱንም ክፍሎች (11 እና 12) የምታነባቸውን መፃሕፍት የገፅ ብዛት ደምር። ከዛ በቀን ሳትጨናነቅ ማንበብ ያለብህን የገፅ ብዛት ወስን! እኔ ሙሉ የማንበብ አቅሜን ተጠቅሜ በቀን እስከ 115 ገፆችን ማንበብ እችላለሁ። በአማካይ በ2 ቀናት አንድ መፅሐፍ መጨረስ እንደማለት ነው! ይህ የሚሆነው ምንም ሳልጨናነቅ በቂ እረፍት (ከ24 ሰአት ውስጥ 7 ሰአት ተኝቼና 8 ሰአት የሚጠጋ እረፍት) ወስጄ ነው። ነገር ግን ይህን ማደረጌ ወደ መጨረሻው የፈተና ሰአት ሊያደክመኝ ስለሚችል አሁን እያነበብኩ ያለሁት ከ40 - 80 ገፅ ነው። መጀመሪያ ላይ አገኘው ከነበረው እረፍት በላይ ጨመርኩ ማለት ነው። እንግሊዘኛን አንብበህ መረዳት መቻልህ በጣም ወሳኝነት አለው። እንግሊዘኛውን ስትችል ነው የምልህን ሁሉ መተግበር የምትችለው፤ በተለይ የላይኛውን የንባብ ሰአት ለ#History, #Economics and #Geography ብታደርገው ይመረጣል። እንግሊወኛውን አንብቦ መረዳት ላይ ችግር ካለብህ ቀድመህ Englishን ግደል። Civics በንባብም በፈተናም ደረጃ ከባድ አይደለም። የ11 እና የ12ን አንብቤ ለመጨረስ የወሰደብኝ 8 ቀን ብቻ ነው። ፈተናዎችንም ስሰራ እስካሁን ከ 86 አልወረደብኝም። Maths በጣም ትኩረት ይፈልግብሃል። ረዘም ያለ ጊዜም ይወስዳል። ስለዚህ የላይኞቹን ካነበብክ በኋላ ከእረፍት ሰአትህ ቀንሰህ 1 or 2 ሰአት ሰጥተህ ተረጋግተህ አንብብ። ካልሆነ ቅድሚያ ትኩረትህን ለአምስቱ subjects (English, Civics, Geography, History and Econimics) ላይ አድርግ። ይህን የምልህ ካለህ የጊዜ ጥበት አንፃር እንደሆነ እወቅልኝ። "Sit and set your goal" የሚባል አባባል አለ። ቁጭ ብለህ የምትጨናነቅበትን ና የምታማርርበትን ጊዜ ብታነብበት እመነኝ ትሰቅላለህ! መጀመሪያ በራስህ ተማመን, ፈጣሪህን ለምን, አጎንብሰህ ተማር, ፕሮግራም አውጣ, ማንበብ ያለብህን የገፅ ብዛት ወስን, ያነበብከውን በራስህ ለመግለፅ ሞክር, ራስህን በፈተና ገምግም! ይህን ሁሉ ማድረግ ከከበደህ ሌላ መፍትሄ ልስጥህ.. ያለፉ የኢንትራንስ ጥያቄዎችን ስራ። ቢያንስ ከ 100 - 200 (የ 2 አመት) ጥያቄዎችን ስራ። 200 ጥያቄ በተአምር ከ 5 ሰአት በላይ አይወስድብህም። በቀን 200 ጥያቄዎችን ብትሰራ ዛሬን ጨምሮ ቢበዛ 30 ቀናት ቢኖሩን 30×200=6000 (60 የፈተና ወረቀቶች) ጥያቄዎችን ሰራህ ማለት አይደለም?! በዚህም የጥያቄ አወጣጣቸውን ማወቅ, ፈተና ሲያወጡ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቦታዎች መለየት ትችላለህ። የሚደገሙ ጥያቄዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ በነፃ እድል መጣችልህ ማለት ነው(ከአንድ የፈተና ወረቀት 2 ጥያቄ ቢያወጡ 120 ጥያቄ በነፃ ሰራህ እንደማለት ነው)። ከትምህርት ሚኒስትርም እየመከሩን ከነበሩ ነገሮች አንዱ ያለፉ የፈተና ጥያቄዎችን እንድንሰራ ነው። ስለዚህ ይህንን አድርግ። በዚህ በርታ። ከልጅነታችን ጀምሮ ይህን ሁሉ አመታት የለፋነውና የተለፋልን ይህች ኢንትራንስ የምትባልን መሰናክል ሊያሳልፈን ካልቻለ መማራችን ከንቱ ነው። ገና ብዙ ከዚህ የበለጡ መሰናክሎች ይጠብቁናል። ይህን ፈተና ከወደቅን ከወደቅንበት ተነስተን አቧራውን ከላያችን ላይ አራግፈን ለሚቀጥለው ፈተና ልምድ ወስደንበት ልናልፍ ይገባል። ኢንትራንስ የአዲስ ህይወት መጀመሪያችን ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የህይወታችን መጨረሻ ሊሆን አይገባም! አይሆንምም!! ብዙ ለፍላፊ ነገር ነኝ። የመከርኩህን ብተገብረው ዘንድሮ ሰቃዩ እኔ እሆናለሁ¡😅😝 @ABMAHD አመሰግናለሁ
Jun 10, 2021