ከራድዮን የሚባለው ወፍ ልዩ/ግሩማን እንስሳት ከሚባሉት ይመደባል..ምክንያቱ ደግሞ፦ ይህ ወፍ በተፈጥሮ ቀለሙ በጣም ነጭ እና አንፀባራቂ ነው..ግብሩ ደግሞ ለታመመ ሰው ፈውስን ይሰጣል። እንዴት? ጠቢባን የዚህን ወፍ ግብር ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ...በአካባቢው የታመመ ሰው ካለ እና በህክምና ፈውስ ካጣ ወደዚህ ወፍ ይወስዱታል ..ታዲያ ይህ ሰው ማይድን/ሟች ከሆነ ወፉ ወደ ሰውየው ሳያይ እና ሳይቀርብ ጥሎት ይሄዳል..የሚድን ከሆነ ደግሞ ተጠግቶ የዚያን ሰው ትንፋሽ ይወስዳል ያኔ ሙሉ ለሙሉ ቀለሙ ወደ ጥቁር ይለወጥና በሮ ወደ ባህር ጥልቅ ገብቶ ለ 3ወር ያህል ይጠፋል ከዛ ራሱን አድሶ ይወጣል......በቀድሞ ዘመን ይህ ወፍ ከነገስታት ቤተ-መንግሥት አይጠፋም ነበር
Jun 09, 2021