የኩላሊት failure 2 ዓይነት ሲሆኑ Acute (ጊዜያዊ) እና Chronic ይባላሉ። ይህም ኩላሊት ስራውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ስራ ሲያቆም በዲያለሲስ (በእጥበት) ይኖራል ማለት ነው። ለበሽታው ምክንያት የሚሆኑት 3ቱ common ነገሮች ከፍተኛ የደም ግፊት/hypertension ፣ስኳር በሽታ፣ እንዲሁም አንዳንድ መድኃኒቶች (በተለይ Anti-painኦች ባይወሰዱ ይመረጣል) ለኩላሊት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ። በተጨማሪም እንደ መጠጥ፣ ሲጋራ፣ illegal አደንዛዥ ዕፅዋት እና የመሳሰሉት የሱስ ነገሮች ለኩላሊት ስለሚያጋልጡ ከነሱ መቆጠብ አስፈላጊ ነው አንዳንድ ድንገተኛ ነገሮችም ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ በአደጋ ወይም በወሊድ ጊዜ ከፍተኛ የደም መፍሰስ ለዚው በሽታ ሊያጋልጥ ይችላል። ይህ ግን ሁሌም የሚሆን አይደለም፥ ለክፉም ለደጉም ግን ጥሩ በሚባል የጤና ተቋም (የክፍለሀገር አብዛኛው አይሆንም😤 ) በመሄድ የደም ምርመራ ማስደረግ ጥሩ ነው። የጉበት caseም ምክንያት ሊሆን ይችላል እንዳንድ rare case ደሞ አለ። ለምሳሌ አንዳንድ የካንሰር ዓይነቶች እና ከደም ጋ፥ በተለይም ከደም መርጋት ጋር ተያያዝ የሆኑት በሽታዎች ምክንያት ይሆናሉ። ብዙ ሰው የኩላሊት failure በሽታ ሲባል ኩላሊት ወይም ጎን አካባቢ የሚያም ነገር ይመስላቸዋል፥ ግን አይደለም። የሚያያዘው ከደም ማጽዳት ጋር ስለሆነ ከመላው አካላት ጋር ነው። የመጀመሪያ አካባቢ ምልክቶቹ ፦ የባሕርይ መለወጥ (ከሰው ሰው ሊለያይ ይችላል)፣ ድካም፣ እንደ ድብርት ያሉ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ.... ከዛም ቀስ በቀስ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ የምግብ ሽታ መጥላት፣ የማሳከክ ዓይነት ስሜት፣ ሌላ በሽታ የሚመስል ዓይነት ምልክት ማሳየት(ታይፎይድ፣ ታይፈስ፣ ጨጓራ፣ የሳምባ ምች/ኒሞንያ).......ወደ መጨረሻ stage ሲደርስ ደሞ ሳምባን ስለሚነካ ትንፋሽ ማጠር፣ እራስን መሳት፣ አክታ መተፋፋት (ብዙ ጊዜ በደም የተቀላቀለ)፣ እስከ ቬንቲሌተርም ሊያደርሰው ይችላል። ከዛ ሲያልፍ ግን ህይወቱን ሊያጣ ይችላል። በዚ ሰዓት ምን እናድርግ፦ እራሳችንን ከጠረጠርን የደም chemistry ምርመራ ማድረግ - ይህ ምልክት እየታየ ከመጣ ወደ ተሻለ የጤና ተቋም መሄድ (የክ/ሀገር ሰዎች ከሆናቹ ቀጥታ ወደ አዲሳባ ብትመጡ ይመረጣል) - ለዲያለሲስ ያልደረሱ ወይም ብሽታቸው ሳይታወቅ በየትኛውም ሁኔታ ምግብ እምቢ አሉ በሚል ሰብብ ግሉኮስ ወይም NS solution እንዳይደርግላቸው መጠበቅ - የPotassium እና urea መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን መከልከል። ቅድም የተመለከታቹት ምልክት ከታየባቹ በፍጥነት ጥሩ ወደ ሚባል ጤና ተቋም ብትሄዱ ይመረጣል፥ አደራ።
Jun 05, 2021