ሰላም! Abadula ነኝ ለተለያየ ምክንያት ከዚ በፊት ለማንሳት ባልችልም ለማንሳት አሁን ላነሳ የምፈልገው አንድ ሃሳብ አለኝ። ብዙ ጊዜ ጤናነክ ጥያቄዎች ሲጠየቁና መልስ ሲሰጥባቸው እስከዛሬ ደርሰናል። ደሞም ባሁን ሰዓት በጣም አስቸኳይ የጤና ነክ ጥያቄዎችን ሰዓት ሳይሰጡበት Approve እንዲደረግ በመደረጉ አድሚኖች ሊመሰገኑ ይገባል። እናም ወደማነሳው ነጥብ ስመጣ፥ በዚህ ቦት እንዳየሁት ከሆነ ዶክተሮችን ጨምሮ በርካታ የጤና ባለሙያዎችና ተማሪዎች ያሉ ቢሆንም #Health ጥያቄ ላይ ያላቸው ተሰሚነት በጣም አናሳ ሆኖ እናገኛቸዋለን።ለማለት የፈለግኩትም እኚ ጤና ባለሙያዎች ለቻናሉ ቁልፍ ሰዎች መሆናቸው የታወቀ እንደመሆኑ አንዳንድ የተለየ ቦታ ቢሰጣቸው ምን ይመስላችኋል? ለምሳሌ፦ 1. የትኛውም #Health ወይም ሌሎችHashtag ላይ ስለጤና የሆኑትን ጥያቄዎች በአድሚን ፍቃድ በቦቱ በኩል ቀጥታ ቢደርሳቸው 2. መጥፎ የጤና ምክር የሚመክሩትን ሰዎች ከተወሰኑ አካውንቶች ጋር በመሆን ሪፖርት ሲያረጉ፥ ኮመንቱን እስከመሰረዝ ሥልጣን ቢኖራቸው 3. ጤና ባለሙያነታቸው ከተረጋገጠ ደሞ በአድሚኖቹ Verified badge ቢሰጣቸው 4) በየትኛውም ሰዓት ቢመልሱ እንደአገልግሎት እርከናቸው፥ Browse ሲደረግ መልሳቸው እንዲቀድም ቢደረግ ቻናሉን ምን ያህል ወደ ተሻለ ቦታ ይወስደዋል ብላችሁ ታምናላችሁ?
Jun 03, 2021ኧረ አሪፍ ሀሳብ። በሰው ህመም እንጨት እየሰደዱ ሚቀልዱ ህፃናትንም እኮ አልቻልናቸውም። በተረፈ ሲንግል ሁነን relationship advice ለምንሰጠውም badge ✅ይሰጠን✊✊😂
Jun 04, 2021