Urgent ሰላም ሰዎች ከ50 በላይ ስንኝ ያለው አሪፍ አማርኛ ግጥም ላኩልኝ አስቸኳይ ነው አመሰግናለሁ 🙏
Jun 03, 2021# እኔነት ፡ የራስ ጥገኝነት እኔነት ምንድነው ንገረኝ አንተ ሰው የኔስ ከታች አለ እስኪ ተመለከተው ስለ ሰው ልጅ ሳስብ እጅግ ይደንቀኛል አንዷም በመሆኔ ደርሶ ይቀፈኛል እኔነት ነግሶብን እኛን ዘንግተነው ለብቻ መጠቀም ባህል አድርገነው አለምን ጠቅለን በኔ ሳጥን ውስጥ አጭቀን ከተነው እንዴትስ ይታየን ለብቻ መክበሩ ትርጉም እንደሌለው ቸልታችን ልቆ ሌላውን ለማየት ሰከንድ እንኳ አተን ሆኖብናል ቅኔ የደስታችን ሚስጥር ጥግ ተሸሽገን ስጋችን ደልቦ ከስቶ ነብሳችን ማስተንተን ተስኖን ብኖር ለዛሬያችን የማስተዋል ጥቅም ከልብ ተሰውሮ በደመነብስ መኖር ከርሞብን ዘንድሮ የምድር ገጽታ መስሎን ሚዘልቀን በወርቅ ተለብጣ ብናያት አምራብን ተማርከን በውሸት እውነት መራበን ባዶዋችንን ቀረን ከሁሉም ስንዘግን መያያዝ ዘቅቶት አይን ከልባችን መስማማት አቅቶት ቀልብ ከአቅላችን ጊዜው ሲቀያየር ባለንበት ዝገን መሽቶ እየነጋ አመታት አለፈን እንኳን ለሰው ልንተርፍ የራሳችን ኮተት ተራራ አክሎ አስሮን ካለ መተት የፈጸምነው ጥፋት አምጥቶብን መአት ለውጥ አንፈልግም አንማር ከስተት ከፈጣሪ በታች ደግፉኝ እያለ ክፉኛ ማጣቱን ነግሮን እየማለ የምስኪኑን እንባ አልፈነው ባላየ የፈጣሪ ቅጣት እንደውም ዘገየ ሌላው ይስራው እንጂ እኔማ ምንአለኝ እሱ ይስጠው እንጂ እኔማ ድሀ ነኝ እሷ ትርዳው እንጂ እኔማ ብር የለኝ እንዳረጉት ያርጉት እኔማ ምን ገዶኝ መራመድ አቅቶት መናገር ተስኖት ወገኖቼ እርዱኝ ባለ አንደበቱ ጠላቶቼ ብሎ አወጣን ካንጀቱ ብሶበት ህመሙ ቢያልፍ ከዚች አለም ከትንኝ አንቆጥረው ምንም አይገርመንም ሰላሳ ኖረ ሀምሳ ደንታም አይሰጠንም ሀምሳ ብር ጠፍቶ ግን ተኝተን አናድርም ዛሬ የኮራነው አንዲት ብር ለመስጠት ምንን ተማምነን ነው ነገን ለመሰንበት ለብሰን የወጣነው በራሳችን ፍቃድ ቀናችን ደርሶብን ይወጣል በሰው ክንድ የደግነት መንገድ አድርገነው እርም ካለፈ ቢገባን ደርሶ ምን ሊጠቅም አሁን ነው መንቃቱ ሳያልፍብን ወቅቱ ከራስ ጋር መታረቅ ክፋትን ማውጣቱ ለኔ ይልቅ በእኔ ይሟላ ጉድለቱ ሽንቁሩ ይደፈን ይዘጋ ክፍተቱ አዛኙ እንዳለው በምድር ላዘነው እኔ አለሁለት እዝነቴን ላለብሰው በየቤቱ ላሉት እኛን ሚጠብቁት በተስፋ ተሞልተው በፍጹም ትእግስት ማን ሔዶ ያንኳኳ አለው ይበላቸው ማነው ተጠያቂ ሄጄ ልንገራቸው የንፉግነት ዛር ሰፍሮብናል መሰል አንተው ጠብቀን ከራሳችን ተንኮል ጌታ ያግራው እንጂ የኛስ ጉድ አያልቅም ከሱ የተጠጋ በፍጹም አይከስርም!! BY-Hypocrite_writer yene new ena idk if will help you idk if is helping or not try to look it
Jun 04, 2021