D/r abiy tenagere yetebalew neger mndnew malet teqenabro new esu altenagerewm mibalew were esti video kehone lakulgn
Jun 03, 2021ከፊል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር 👆 ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ የተባለውና ከብልፅግና ስብሰባ ተደብቆ/ሾልኮ ወጣ ተብሎ ውጭ ሀገር ባሉ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ በሚሰሩ የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጨው የድምፅ ፋይል የተቀነባበረ መሆኑን የጠ/ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ትላንት አሳውቋል። ከድምፅ ፋይሉ ጋር በተያያዘ በርካቶች የራሳቸውን ማብራሪያ እየሰጡ የሚገኙ ሲሆን አንዳንድ ጋዜጠኞች እና የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም በቻሉት አቅም ተቆራርጦ ተቀጥሏል ያሏቸውን ንግግሮች አንድ ላይ አቅርበው ግንዝቤ ለመፍጠር መሞከራቸውን ተመልከትናል። ሾልኮ ወጣ የተባለው የድምፅ ፋይል በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከተሰራጨ በኃላ በሚሊዮን የሚቆጠር ተከታይ ያላቸው የፌስቡክ ገፆች ፣ ታዋቂ ሰዎች ፣ አክቲቪስቶች ፣ የኢትዮጵያ መንግስትን በመቃወም የሚታወቁ የውጭ ሀገር ግለሰቦች ሲቀባበሉት አምሽተዋል። አንዳንዶቹ ቆየት ብለው ባደረባቸው ጥርጣሬ ፋይሉን ከገፃቸው ላይ ለማንሳት መገደዳቸውን ፅፈዋል። ከላይ የተያያዘው የ41 ሰከንድ ቪድዮ በከፊል ጠ/ሚ ተናገሩ የተባሉትን ቃላት እና አረፍተነገሮች የያዘ እና እንዴት ቃላት እንደተቆራረጡ ለማሳያነት JONA.G በተባለ ግለሰብ የቀረበ ነው። @tikvahethiopia