Loco163
#entertainment
እቴ ይስጥሽ ከቁመቴ ከላዬ ቀንሶ ያሳድግሽ አንቺን እኔን አሳንሶ . . . ሚለው ግጥም ያላችሁ🙏🏽
May 27, 20213 engagements
እቴ ይስጥሽ ከቁመቴ ከላዬ ቀንሶ ያሳድግሽ አንቺን እኔን አሳንሶ . . . ሚለው ግጥም ያላችሁ🙏🏽
May 27, 2021◎◌◎ይሰጥሽ◌◎◌ ፨ገጣሚ እና አቅራቢ ፦በእውቀቱ ስዩም @books_worldd #ሼር
ይስጥሽ (በዕውቀቱ ስዩም) እቴ… ይስጥሽ ከቁመቴ ከላዬ ቀንሶ ያስረዝምሽ አንቺን እኔን አሳንሶ ከሰጎን እረዝመሽ ስትቆሚ ከጎኔ ቁመቴን መጽውቼሽ ጫጩት ላክል እኔ፤ ይስጥሽ ከጸጉሬ ከአናቴ ላይ ዘግኖ ይገጠብ ራሴ ያንቺ ተጎንጉኖ አወይ ጸጉሯ ብለው ኮረዶች ሲያወሩ ድጥ ራስ ነህ ብሎ ይዝለፈኝ ሰፈሩ፤ እቴ… ይስጥሽ ከወዜ ላይ ጨልፎ ከፊቴ ይቅዳልሽ ከደሜ ጠልቆ ከጅማቴ ከአይን ያውጣሽ እያለ ሲመርቅ አድናቂ እስቲ እግዜር ይማርህ ይበለኝ ጠያቂ። እቴ… እጄን ብትፈልጊ እግሬን ብትፈልጊ አንገቴን ደረቴን ተሰጥኦ ሀሳቤን ያደምቀኛል ብለሽ ያሰብሺውን ሁላ እግዜር ከኔ ወስዶ ከሰጠሽ በኋላ ያስቀርልኝ አይኔን አንቺን ማየት ብቻ ያኖረኛል እኔን።
May 27, 2021I don't have it but if it helps its bewketu siyoum's poem
May 27, 2021