ምንም አላገኘሁበትም ከጠቀመኝ ያጣሁት ይበልጣል የመጨናነቄን ያህል ምን አወኩ? በራሴም ሆነ በሀገር ላይ ምን ለውጥ አመጣሁ? ምንም። በጣም ጎበዝ የሆነ ተማሪ ተመርቆ ሲወጣ በስራ ላይ በምንድነው የሚለካው? ሰአት አክብሮ በመግባቱና በመውጣቱ ነው፤ አዲስ ነገር በመፍጠርህ ሳይሆን ሰንጠረዥ በሞላኸው ልክ ነው የሚለካው፤ ሌሊቱን ምርጥ የተባለ ስራ ስትሰራ አድረህ ጠዋት አርፍደህ ቢሮ ብትገባ ቅጣት ይጠብቅሀል፤ ምክንያቱም የስራህ መለኪያ ውጤትህ ሳይሆን ሰዐትህ ስለሆነ "ቡርሀን"
May 25, 2021