ሰላም .... የኢትዮጵያ የቀድሞ የጦር እና ስልጣን ሹመት ዝርዝር በቅደም ተከተል የሚነግረኝ ካለ .. ማጣቀሻችዉን አብራችሁ ብትገልጹልኝ ደስ ይልኛል .. አጼ ፣ ደጅ አዝማች . የመሳሰሉትን ማለቴ ነዉ
May 22, 2021#1 #ዣን - ዣን ማለት ለንጉስ የሚሰጥ ማእረግ ነው። ዣንሆይ ሲባል እንደሰማችው አልጠራጠርም። ዣን ማለት የሁሉ የበላይ ማለት ነው የሁሉም! ለንጉሰ ነገስት ብቻ የሚሰጥ ማእረግ ነው። #2 #ልጅ - ይህ ማእረግ የሚሰጠው ለንጉሱ ልኡላውያን ቤተሰብ ላለ ብላቴና ብቻ ነው። ንጉሱ በድንገት ቢሞት ቀጣይ አልጋ ወራሽ ወይም ንጉስ የሚሆነው ልጅ ተብሎ የተሰየመው ህፃን ልኡል ነው። የልጅ እያሱን ታሪክ እናስታውስ #3 #ባላምባራስ/ ራስ - ይህ ማእረግ የሚሰጠው ከንጉሱ ቀጥሎ የማዘዝ ስልጣን ላለው ሰው ነው። ባላምባራስ ማለት የአንባው ራስ ወይም የአንድ ክፍለሃገር መሪ ማለት ነው በጦርነት ግዜ ንጉሱ ክተት ሲጠሩ የሁሉም ጦር አዛዦች የበላይ አዛዥ ሆኖ ይዟቸው ይመጣል ከሱ ስር ያሉት አዛዦች እሱ እሚሰጣቸውን ትእዛዝ ይቀበላሉ። ባላምባራስ ደስታ፣ ራስ አሉላ #4 #አዛዥ - ከስሙ እንደምንረዳው ከባላምባራሱ ቀጥለው ያሉ ብዙ ጦር አዛዦች ናቸው ጦሪን ይመራሉ። አዛዥ ለጥይበሉ #5 #ፊትአውራሪ - ይህ ማእረግ የሚሰጠው ጦሩን ከፊት ሆኖ ለሚመራና ለሚያዘምተው አለቃ ነው። በስልጣን ተዋረድ መሃል ላይ ቢገኝም ከሁሉም ግን ክብር የሚሰጠው ለፊት አውራሪ ነው የጠላትን ጦር ሳይፈራ ከፊት ቀድሞ እየመራ ይዋጋል። ፊት አውራሪ ፊላቴ #6 #ደጃዝማዥ - የአንድ ክፍለጦር አዛዥ ሲሆን ከሃገር ውጪ ሄዶ ጦሩን የሚያዘምት ማለት ነው። ደጃዝማች እንዳለው #7 #ቀኝ አዝማች - ይህም የአንድ ክፍለጦር አዛዥ ሲሆን ጦሩን በቀኝ በኩል የሚያዘምት ነው። ቀኝአዝማች የትምጌታ #8 #ግራ አዝማች - ከቀኝ አዝማች ጋር ተመሳሳይ ስራ ቢኖረውም ከቀኝአዝማች ትንሽ ዝቅ ያለ ስልጣን አለው። በግራ በኩል ያዘምታል ቀኝ አዝማች ግራ አዝማችን ማዘዝ ይችላል። #9 #ቀኝጌታ - ብዙ ግዜ ይህ ማእረግ የሚሰጠው ለንጉሱ የቅር አማካሪዎች ወይም ቤተዘመዶች ነው። ንጉሱን ያማክራሉ ነገርግን በምንም አይመት የጦር አውድማ ላይ አይሳተፉም። ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ #10 #ዣንጥራር - ይህ ማእረግ ደግም የሚሰጠው ከጦሩ ኃላ ሆኖ ነጋሪት እያስጎሰመ የጦረኛውን ወኔ የሚያነቃቃ የጠላትን ጦር ልብ ለሚያሸብር ሸላይ አለቃ ነው። ይህንን ይመስላል እንግዲ ቀደምተከተላቸውም እንደተቀመጠው ነው መጀመሪያ ዣን አለ ከዛ ልጅ፣ ራስ፣ አዛዥ፣ ፊት አውራሪ፣ ደጅ አዝማች፣ ቀኝ ወይም ግራ አዝማች፣ቀኝ ጌታ ወይም ጌታ፣ ዣንጥራር። አንድ የንጉስ ዘር የሌለበት ጎበዝ ጦረኛ በንጊሱ ፈቃድ እስከ ራስነት ድረስ ሊሾም ይችላል ከንጉሱ ቀጥሎ ያለው ታላቅ ማእረግ ነው የንጉሱ ቀኝ እጅ እንደማለት ነው። የንጉሱ ዘር ከሆነ ደግሞ ልኡል ወይም ልጅ ይባላል እድሜው ገና ከሆነ በንጉሱ እልፍኝ ያድጋል የንጉሱ ልጅ ወይም የልጅ ልጅ። ልጅ ከሌለው የወንድም የእህት ልጅ ሊሆን ይችላል ንጉሱ የመረጠው ልጅ አልጋ ወራሽ ወይም ቀጣይ ንጉስ ይሆናል። Ye atse mnmn alagnehume yagnehulh yehenen nw
May 22, 2021