Hi, BreathzTruth ወይም "እውነትን ብቻ ለመተንፈስ የወሰነው" ልጅ ነኝ Ethiopia ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚከበሩባት ሀገር ነች(መሆን አለባት) የሚሉ ሰዎች እየበዙ ነው። በዚህም ድሮ የነበረው መለኮታዊው ስርዓት ሁሉንም ብሔር እኩል ስላላደረገ እሱን ንዶ ሁሉም የሚከበርባት ኢትዮጵያን አዲስ እንፍጠር እየተባለ ይገኛል። በዚህም ሁሉም ብሔሮች ያሉበትን ማንነት ማንፀባረቅ priority ይሰጠው በተባለው መሰረት....ኦሮሞው የኦሮሞ ማንነቱን እንዲያንፀባርቅ እና በቋንቋው #ብቻ እንዲጠቀም፣ ትግራዩ፣ ደቡቡም... ወዘተ እንዲህ እንዲያደርጉ ተገደው አሁን ሁሉም በየራሳቸው አለም ላይ ናቸው። አሁን ደግሞ አማራው ለብሔሩ ብቻ እንዲቆም ተገዶ እሱም በራሱ አለም ላይ እየዞረ ይገኛል። ሁሉም የየራሱን ማንነት ፈጥሮ የሌላውን እንዲፀየፍ #ተሰርቶበት ግን ደግሞ "ኢትዮጵያን ሁሉም ብሔሮች የሚከባበሩባት ትሆናለች" እየተባለ ይደሰኮራል ጥያቄዬ ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች ናት ወይስ የኢትዮጵያኖች? የብሔር እኩልነት "ተበድለው ነበር" ተብሎ የሚነገርላቸውን ማንነቶችን በማንፀባረቅ የሚመጣ ነው? የድሮው የኢትዮጵያ ስርዓት ብሔሮችን ያዋደደና አንድ ያደረገ አልነበረም? NB: የኔ ሀሳብ፣ ሲጀመር ኢትዮጵያ የማን እንደሆነች አላወቅንም ወይም ደግሞ እንደ fake ethiopianistኦች ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ከማለት በቀር ማን እንደሆነች አልተረዳንም!
May 19, 2021Well. በኢትዮጵያ ምቼ መለኮታዊ አስተዳደር እንደ ነበር ግራ የገባኝ ቢሆንም ሌሎቹን ወደ መመልስ ልሂድ... አዎ እኔም ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች ስብጥር እና ሁሉም በየማንነቱ የምከብርባት ሃገር ልትሆን ይገባል ከሚሉ ፌዴራሊስም አዲዮሎጂስት ሰዎች አንዱ ነኝ። ግን ለማስተካከል ያህል ማንም ሰው በራሱ ግዛት ቋንቋ የመገልገል እና የማገልገል መብት እንጂ የራሱን ብቻ ማለት እንዳልሆነ Bilinguals የሆኑ ሰዎችን ማየት ብቻ አስፈላጊ ነው እንደ ማስረጃ ያክል። እናም ይህ ማንነት አዲስ የተፈጠረ ሳይሆን ጥንት ለማፈን የተሞከረ፤ ግን ከቤተሰብ የተወረሰ፣ የደም ሥር ውስጥ የሚዘዋወር ማንነት መሆኑ መዘንጋት የለበትም። እና ኢትዮጵያ የማናት የሚለውን ጥያቄ መልስ የሚሆንልህ "ከሁሉም ብሔር ብሔረሰብ የተገኙ የኢትዮጵያውያን ሀገር ናት" እነዚን 2ቱን መነጠል በፍጹም የማይቻል መሆኑን እየተረዳን እንሂድ። የብሔር እኩልነት "ተበድለን ነበር" የሚለውን በማንጸባረቅ ሳይሆን የደረሰባቸውን በደል Deny ባለማረግ እና መጪውን መፍትሔ በማበጀት ነው! የድሮው ሥርዓት ብሔር ከብሔር ሃይማኖት ከሃይማኖት ያጋጨ እንጂ ያቀራረበ አይደለም። እዚ ላይ ማብራርያ ከመስጠት በፊት ግን ለማዳመጥ ዝግጁ መሆኑ በጣን አስፈላጊ ነው።
May 19, 2021