#politics አንድ ጥያቄ ለሃገራችን ክርስቲያኖች‼ «ከፍልስጤም ይልቅ እስራዔልን የምትደግፉት ለምንድን ነው⁉️» ወደ ኃይማኖታዊ ጉዳይም እንግባ ከተባለ፤ አይሁዶች የአላህን ነቢይ ዒሳን (ሰላም በርሱ ላይ ይስፈንና) "የዝሙት ልጅ ነው!፣ ሐሰተኛው እየሱስ ነው!፤ ትክክለኛው እየሱስ ገና ወደፊት ይመጣል!" ብለው ነው የሚያምኑት። ክብሩን በጣም ነው የሚያጎድፉት። እንደ እኛ ሃገር ክርስቲያኖች ደግሞ፤ እየሱስ አምላካችን ነው ብለው ያምናሉ። ይህንን አምላካቸውን የሁዳ እንደሰቀለባቸውና እንደገደለባቸው ያምናሉ። በቀራኒዮ ላይ ክፉኛ እንዳሰቃዩባቸው ያምናሉ። እኛ ሙስሊሞች ግን ነቢዩ'ል-ሏሂ ዒሳ (እየሱስ) (ሰላም በርሱ ላይ ይስፈንና) የተከበረ የአላህ ነቢይና መልዕተኛ መሆኑን እናምናለን። እርሱ የአላህ የተወደደ ነቢይ መሆኑን ያላመነ ሙስሊም ጀነት አይገባም ብለን እናምናለን። እናቱ መሪዬምም (ማርያም) እኛ ሙስሊሞች ዘንድ እጅግ በጣም የተወደደችና ትልቅ ቦታ ያላት እንቁ ሴት ናት። አይሁዶች ግን በጣም ይጠሏቸዋል። እርሷንም ዝሙት ሠርታለች ብለው ያምናሉ። ታዲያ ለምን⁉️ (በእናንተው አስተሳሰብ መሠረት) እንደት አምላካችሁን የሰቀሉና የገደሉ ሰዎችን ትደግፋላችሁ?! አምላካችሁን ከሚያንቋሽሽ፣ ከገደለና ከሰቀለ ህዝብ እና ነቢይ ነው ብሎ አምኖ ከነ እናቱ ከሚወደውና ከሚያከብረው ህዝብ የትኛው ቀርቧችሁ ነው? መልሳችሁን እሻለሁ!
May 18, 2021Actually I don't support Israel's deed. ግን ክርስቶስ የተገረፈው የተሰቀለው እና የሞተው በአይሁዶች ፍቃድ ሳይሆን በእራሱ ፍቃድ ነው። ስለዚህ ክርስቶስ ሰቀሉ ብሎ መጥላት ክርስቲያናዊ አይደለም። አዎን አሱንም ስሙን እንደሚያቋንሽሹት በእርግጠኝነት ይታወቃል። ከአይሁዳውያን ይልቅ ፍልስጤማውያን የክርስቶስን መለኮታዊነት የሚያምኑ ናቸው። ግን የኔን ሃሳብ ልንገርህ፥ እስራኤላውያን መጥላቱን ትተው ለምን እንደ ብራዚል ሃውልቱን በኢየሩሳሌም አይተክሉለትም፥ ትክክል ካልሰሩ ምንም የሚደገፉበት ምክንያት የለም። በአሁን ሰዓት በማን ጎን ነው የምትቆመው ብትለኝ በፍልስጤም ጎን ነው። በነሱ ጎራ የሆንኩኝ ግን እነሱ ትክክል ስለሆኑ ወይም ስላልሆኑ ሳይሆን በዙ ሴቶቻቸው እና ህጻናት ስለተገደሉባቸው ነው። ግን ሁለቱንም የምደግፍበት ምክንያት የለም! ኃይል ስላጣች እንጂ እስራኤል ያደረገችባትን ግፍ ፍልስጤምም ብትሆን የማታደርግበት ምክንያት አይኖርም።
May 18, 2021