Esti guys mechem yematresut be chikoch fit yagatemachun wordet nigerugn Just fun lemareg
May 15, 2021አንድ በጣም የምታስጠላኝ አክት የምታበዛ ልጅ ነበረችና ደብዳቤ ሊልክላት ወሰነ ጀለስ ያው ወዷት ማለት ነው ከዛ ድንገት አሞት ወደቤት ሊሄድ ሆነ ከዛ ለ ሌሎች ጓደኞቻችን እንዲሰጡለት ጠየቃችው እንደማይሆን ሁሉም ነገሩት እሱ ደሞ ከዛ ቀን እንድያልፍ አይፈልግም ለዛ ምስኪኑን እኔን ስጥ ብሎ በግድ በጭቅጭቅ ሰቶኝ ሄደ ከዛ ኮስተር ብዬ ክላሷ ሄድኩና አስጠርቻት ከ ደረት ኪሴ አውጥቼ እንኪ ለብቻሽ አንብቢው ብሎሻል ብዬ ሰጠህኡአት/ይሄን ሁሉ ሳደርግ እያየኋት አልነበረም/ከዛ ኮስተር እንዳልኩ ወደክፍሌ ሄድኩ ከዛ ትንሽ ቁጭ እንዳልኩ ጀለሶች ወደኔ እየሳቁ መጡ ምንድነው ስላቸው አንተ ውርደታም ዝም በል የፈተና ወረቀት እኮ ነው የሰጠሃት አሉኝ ከዛ የደረት ኪሴን ቼክ ሳደርግ ደብዳቤው እኔ ጋር ነው ለካ 3/10 ያመጣውትን ፈተና ነው የሰጠዋት ቶሎ ሄጄ ደብዳቤውን በድጋሚ ለብቻሽ አንብቢው ብዬ ስሰጣት እሱ አይመለከትህም ብላ ገላምጣኝ ሄደች ምንም ሳልመልስላት ወደክፍል ሄድኩና ሳስበው ለካ ውርደት ነው
May 16, 2021