#Urgent Ere guys help🙏, semonun tonsil yzogn neber still altewegnm gn ke tlant mata jemro guroroyen ykerekregnal ena sal(derek sal) yaslegnal, is it because of the tonsil shit or lela chgr ale?😳 I'm worried😟
May 15, 2021✍️ #የጉሮሮ #ህመም #ሁሉ #ቶንሲል #ነው #ብለው #ያስባሉ? 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ 👉👉 #የተከበራችሁ የገጻችን ተከታታዮች የቶንሲል ህመም የምንለው ከእንጥል በጀርባ በቀኝ እና በግራ በኩል የሚገኙ የጎሮሮ ክፍሎች ተቆጥተው በሚያብጡበት ጊዜ ነው፡፡ 👉👉 #የቶንሲል ህመም በብዛት በቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት ሲሆን አልፎ አልፎ ደግሞ በባክቴሪያ የሚመጣበትም ወቅት አለ፡፡ 👉👉 #የቶንሲል ህመም ምን አይነት ምልክት አለው? 📌 ራስ ምታት 📌 መጥፎ የአፍ ጠረን 📌 ትኩሳት 📌 አብጦ የቀላ ቶንሲል 📌 አንገት አካባቢ እብጠት መታየት 📌 ለመዋጥ መቸገር 📌 ቶንሲል አካባ ነጣ ነጣ ያሉ ነገሮች መታየት ናቸው፡፡ 👉👉 #የጉሮሮ ህመም በእርግጥ ዘርፈ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም ነገር ግን ጉሮሮዎትን በታመሙ ቁጥር ሁልጊዜ መንስኤው ቶንሲል ላይሆን እንደሚችል መገንዘብ የግድ ይላል፡፡ ታዲያ መንስኤው ምን ሊሆን ይችላል? 📌 የጉሮሮ አለርጂ 📌 ጉንፋን 📌 የጨጓራ አሲድ መረጨት 📌 አስም 📌 የሳይነስ ህመም 👉👉 #እንደአጠቃላይ የጉሮሮም ይሁን የቶንሲል በሽታ ሲያጠቀን ምን ማድረግ ይኖርብናል? 📌 በሙቅ ውሀ እና በጨው ጉሮሮን ማጠብ 📌 ቀዝቃዛ ምግቦችን እንዲሁም መጠጦችን ማስወገድ 📌 የዝንጅብል ሻይ መጠጣት (በጨጓራ አሲድ የመጣ ካልሆነ) 📌 ውሀ በደንብ መጠጣት 📌 ቅዝቃዜ እና ንፋስ መጠንቀቅ 📌 እንዲሁም ነጭ ሽንኩርት መመገብ 📌 በተለይም በአመት በተደጋጋሚ ከ7 ጊዜ በላይ የሚከሰት የቶንሲል ችግር ካለ የግድ ወደ ህክምና መሄድ ይኖርቦታል፡፡ 👉👉 #ጉሮሮዎት አካባቢ የህመም ስሜት አሎት?ከዚጋር የተያያዙ ጥያቄዎች እና ስለማንኛውም የጤና ጉዳዮች ላይ መማከር ካሻዎ 8809 ይደውሉ ከጤና ባለሙያዎች ጋር ይማከሩ !! ከሰኞ እስከ ሰኞ ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ሊያማክሩዎት በመስመር ላይ ይገኛሉ!!! (#በጤና #ባለሙያ #ሄርለም)
May 15, 2021