Guys oneg shene adiss ababa gebtual mibalw mn yahl ewnet nw??
May 15, 2021Actually ከመንግሥት በስተቀር ሸኔ exactly ምን እንደሆነና ማን እንደሆነ የሚያውቅም "ሸኔ" ማለት ቃሉ ምን ማለት ነው? ሸኔ የአፋን ኦሮሞ ቃል ሲሆን ሸን/አምስት ማለት ነው። ሸኔ ደሞ አምስቴ/አምስተኛ እንዲሁም አንድ-ለአምስት ቡድንም ሸኔ ይባላል። ስለዚህ በትርጉም ደረጃ ከጦር ጋ ምንም ግንኙነት የለውም። ግን ልክ ለአይሁዳውያን 12 እና 7ቁጥር ፍጹም ምልክት እንደሆነ ለኦሮሞ ደሞ 5 እና 9 (ሸኔ እና ሰግሌ) ሲሆን፥ 5ቱ ኦዳ፣ 5ቱ ቦኩ፣ 5ቱ ገዳ ኦሮሞ፣ 5ቱ የኦሮሞ ቅርንጫፍ፣ 5ቱ ጎጌሳ ኦሮሞ (5ቱ የኦሮሞ ገዳ ፖለቲካ ፓርቲ) ወዘተ... ናቸው። አሁን ትርጉሙን አለዋወዋጡት እንጂ ከጎጥ አስተዳደር ስር የ5 ሰዎች ቤተሰብን ጉዳይ አስፈጻሚም ሸኔ ይባላል። በትምህርት ቤትም የአንድ ለአምስት ሰብሳቢም የሸኔው አለቃ ይባላል። "ሸኔ" በፖለቲካ ውስጥ ምንድነው? በኦሮሞ ገዳ ሥርዓት ውስጥ ከጉሚ ጨፌ (ጠቅላይ ፓርላማ) ስር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሸኔና ሰግሌ በመባል ይታወቃሉ። ሰግሌ 9ኙ የሚንስትሮች ስብሰባ ሲሆን ሸኔ ደሞ የ5ቱ ዋና ዋና ሚንስትሮች ጉባኤ ነው። እናም ኦነግ ሸኔም ሲባል አንድ የታጠቀ ቡድን ማለት ሳይሆን ኦነግ ጉሚ ሸኔ (5ቱ የኦነግ ጉባኤ) ማለት የኦነግ 5ቱ ዋና ዋና ማእከላይ ኮሚቴ መሪዎች መጠሪያ እንጂ መንግሥት የሚለውን አይደለም። በትርጉም ደረጃ ይህ በመሆኑ ንጉሥ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ በሚለው እንጂ Defaming በሚለው በፍርድ ቤት የሚያስከስስ ስም ማጥፋት ነው። አሁን "ኦነግ ሸኔ" ብሎ እየተጠራ ያለው ማንን ነው ታዲያ? በግልጽ አይታወቅም። መንግሥት officially የሚለው በጃልመሮ የሚመራውን የWBOን ክንፍ ነው። WBOም ስሙንም ሆነ ድርጊቱን አይቀበሉትም፣ ጨምረውበትም ያወግዙታል። በሌላው ጎን ደሞ ማንኛውም ጸረ-ብልጽግና የሆነ ሰው ሸኔ ይባላል። በተጨማሪም ሰው ከገደሉና ብሔሩ ላይ በመመስረት ስም ይሰጥበታል፥ የሞተው ኦሮሞ ከሆነ ኦነግ ሸኔ ነው፥ የተገደለው ሌላ ብሔር ከሆነ ደሞ በኦነግ ሸኔ ተገደለ ይባላል። 3ተኛም ደሞ ህዝቡ ሸኔ ነው ብሎ የሚያምነው የትኛውንም አካል ሳይሆን የመንግሥት አካላት የWBO ደምብ ልብስ እና የውሽት ጕንጕን (dread) በመልበስ ህዝብን የሚፈጁ የኦሮሚያ እና የፌደራል ምልምሎች ናቸው ብለውም ያምናሉ። ስለዚህ ሸኔ የሚባለው ማንን እንደሆነ እንኳ ግራ የተጋባን ዓይነት ነን።
May 16, 2021