#እስቲእንወያይበት 1.አሁን የኢትዮጵያ አንድነት ከዚ ጋር በምን ያገናኘዋል። ሁሉም ሀገሩን ይወዳል(ከኔም ጭምር) ነገር ግን ኢትዮጵያ አንድ የምትሆነው ከላይ ፎቶው ለይ እንደተያያዘው በስሌቱ መሰረት 9 ስለመጣ ነው ወይስ በመቻቻል በመቀራረብ ..... ነው አንድ ልትሆን ምትችለው? እናንተ ምን ይመስላቿል...! ? ስለዚህ ሰውስ ያላቹ ግንዛቤ ምንድነው? እኔ ለምሳሌ መጀመርያ በፃፈው መፅሀፍ ስለተጨበጨበለት ጭብጨባው መስመር ያሳተው ነው የሚመስለኝ..? ምክንያቱም የአንዲት ሀገር መፍረስ እና አለመፍረስ ከህዝቦች ፍላጎት አንፃር እንጂ ከቁጥር ጋር ሚያገናኘው አይመስለኝም...! ሀሳባቹን አጋሩኝ! #እስቲእንወያይበት
May 13, 2021ልክ ነው ልክ አይደለሙን ልተወው እና አንድ ነገር ልጠይቅዎ ታሞ ለተኛ እና በተኣምር ለሚያምን ሰው ፈጣሪ ተኣምር አድርጎለት ሲድን በህልምህ እንዳየህ ብትነግረው ወይም እምነት ብለህ ንጹህ አፈር( እምነት አፈር ነው እያልኩኝ አይደለም) ብትቀባው እና ይህ ሰው ቢድን ያደረከው ነገር ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? ልክ መሆን አንድ ነገር ነው ግን ሊፈርስ ያለ የሚመስልህን ቤት በቃል(ንግግር) እና በ እምነት ማጠንከር ብንችል ብናደርግ ምን ችግር አለው? የዚህ ሰው ስራም እንደዛ ይመስለኛል... ደሞ ሌላ ሌላ ነገር ውስጥ ባንገባ ጥሩ ነው ከምንረዳው የማንረዳው ይበልጣልና።
May 14, 2021