Hey everyone. I wanna to ask how the feeling is in ur first day of unv class.
May 12, 2021የተመደብኩበት block ደርሼ ፣ የዶርሜን በር (white house F #45) ከፍቼ ገባሁ ። እንዴት እንደ ሚያስጠላ idea'ው የላቹም ። ተሳስቼ ሽንት ቤት የገባሁ ነበር የመሰለኝ ። ዶርም መሆኑን ያወኩት አልጋና ሎከር በመኖራቸው ነው ። ከሁሉም ግን ድንቅ የሚለኝ ፡ ሽንት ቤቶቹ እንዳለ ቀለም ተቀብተዋል ። የምናድርበት ዶርም ግን ለመጨረሻ ጊዜ ቀለም የተቦረሸው ለመጀመሪያ ጊዜ ይሄ ጊቢ ሲመሠረት ነው ። ግድግዳው የወፍጮ ቤት ይመስላል ፣ ፍራሾቹ ደርቀው ከድርቆሽ በላይ ጠንክረዋል ፣ ሎከሮቹ ተሰባብረው የማገዶ እንጨት መሥለዋል ፣ ኮርኒሱ ኩሽና ይመስል ጠቁሮ የጨለመ ሰማይ ሆኗል ፣ ሊሾው አፈር ለብሶ ወደ መሬትነት ተለውጧል ። በቃ ምን ልበላችሁ ...? ፡ ዶርሙ ከዶርምነት ተራ ወጥቶ ዱሪዬ ዶርም ሆኗል ። እዚህ ውስጥ እየኖርኩማ እንኳን ትምህርት ሊገባኝ ቀርቶ እንቅልፍ እራሱ የሚወስደኝ አይመስለኝም ። አማራጭ የለኝም ፤ ጠልቼ በግድ አንዴ ገብቼበታለሁ ። በጣም ደክሞኝ ስለነበር ፣ በዛላይ ጊቢው ስለዘገነነኝ ዶርሜን ዘግቼ አልጋ ላይ ፌንት ሰራሁ ። (ፌንት ግን ይሰራል ወይስ ይወደቃል ...?😳) ። ይሄን የመሠለ ዶርም ውስጥ ሆኜ በየት በኩል እንቅልፍ ይውሰደኝ...? ። anyways ቤት ሳይሆን ዱር እንዳደርኩ እቆጥራለሁ ። ኧረ ዱር እራሱ በስንት ጣዕሙ ። እውነት አያ ጅቦ እዚህ ቢመጣ "እኔን ፡ እኔን ፡ ምን ሆነክ ነው ጎዳና ላይ የምታድረው...? ፡ በል ተነስና ወደ ቤቴ ልውሰድክ" እንደ ሚለኝ አልጠራጠርም...😕
May 12, 2021