Hey everyone What culture, tradition, norm, custom, celebrations of Ethiopia that you have/haven't practiced and would love to do it and/or be part of it? Thank you so much!🌻
May 11, 2021Yenat abat eger mateb
May 12, 2021Hey everyone What culture, tradition, norm, custom, celebrations of Ethiopia that you have/haven't practiced and would love to do it and/or be part of it? Thank you so much!🌻
May 11, 2021Yenat abat eger mateb
May 12, 2021ትግራይ - አሸንዳ፣ መሥቀል ጎንደር - ጥምቀት አፋር - ዳሎል, The dancing fountains of volcano ሀመር - bull jumping ceremony ጉራጌ - መሥቀል ቢሾፍቱ - ሆራ አርሰዴ (ኢሬቻ) ሐረር - feeding hyenas
May 12, 2021ሀመር😋
May 12, 2021Traveling with the salt traders in Afar might be cool
May 12, 2021ከኩሪፍቱ ሪዞርት ወተን እየሄድን እያለ መንገድ ላይ አንድ ወንድ አንዲትን ሴት በጥፊ መቷት ሲሄድ ሁለታችንም ፈዘን ቆመን ቀረን ። በዛ በኩል እያለፉ ያሉት ሰዎች ሁሉም ባላዬ አለፏት ። እንደውም በልባቸው "እሰይ ፡ ይበልሽ" ያሉ ነው የሚመስሉት ። ይሄን ሳይ አንድ የኦሮሞ ህዝብ ባህል እና የገዳ ሥርዓት ትዝ አለኝ ። እንዲህ የሚል "ባሏ ሰክሮም ይሁን በሆነ አጋጣሚ ሚስቱን ከደበደበ መጀመሪያ የተመታችው ሴት/ሚስት የድረሱልኝ ድምፅ ዕልልታን በሚመስል ዜማ ኤሌሌሌሌሌ እያለች ታሰማለች ። ወድያው ድምጿን የሰሙ ጎረቤቶች ደርሰውላት ከባሏ ያስጥሏታል ። ቀጥሎም ያስጣሏት ሴት ጎረቤቶች የተመታችውን ሚስት/ሴት ይዘው በየ ሰፈሩ እየዞሩ በቅድሙ የድረሱልኝ ዜማ ኤሌሌሌሌሌ እያሉ ድምፃቸውን ያሰማሉ ። ይሄን ድምፅ የሰማች ማንኛዋም ሴት መብቷን ለማስከበር ከቤት እየወጣች ሰልፉን መቀላቀል ይኖርባታል ። ድምፁን ሰምታ ነገር ግን አሻፈረኝ ብላ በሯን የዘጋች ሴት ከተገኘች ሰልፈኞቹ ቤቷ ድረስ በመግባት ይዘዋት ይወጡና "እንዴት ለመብትሽ በርሽን ትዘግያለሽ ፡ አንቺላይ ቢደርስ በሚወጡልሽ ሴቶች ላይ ለምን እንደዚህ ታደርጊያለሽ" ብለው ይገስጿታል ። ያቺ ሴትም ተፀፅታ ይቅርታ ጠይቃ ሰልፉን ትቀላቀላለች ። ላጠፋችው ቅጣት ደግሞ ሴቶቹ ቤቷ ውስጥ በመግባት ቅቤና ወተት ይወስዱባታል...✌️
May 12, 2021ሌላው ነገር ደግሞ ሰልፉን ለመቀላቀል ስትሄድ ባሏ ከከለከላት እሱም በገዳ ሥርዓት መሠረት ቅጣት ይቀበላል ። ሴቶቹ በየ መንደሩ እየዞሩ ሁሉንም የሰፈሩን ሴቶች "እከሊት ስትመታ አልሰማሽም ወይ ፡ እህታችን ጥቃት ሲደርስባት ዝም ትያለሽ ወይ...!" እያሉ ከሰበሰቡ በዋላ ወደ ተደበደበችው ሴት ቤት ተመልሰው በር ላይ ተቀምጠው የተለመደ ድምፃቸውን ያሰማሉ ። ኤሌሌሌሌሌሌ ...!!! ይሄን ጊዜ ድምፃቸውን የሰሙ የሰፈሩ አባገዳዎችና ሽማግሌዎች ዛፍ ስር ተሰብስበው ምንድነው የተፈጠረው እያሉ ይነጋገራሉ ። ቀጥለውም ችግሩ ወደ ተፈጠረበት ቤት ሄደው ከሴቶቹ መረጃ ይወስዳሉ ። በመረጃው መሠረትም ችግሩን አደረሰ የተባለው ግለሰብ ተፈልጎ ይጠራና ምን እንደ ተፈጠረ በግልጽ ያስረዳል ። ከዛን ከአባቶቹ ምክርና ተግሳጽ ይወስድና ሴቶቹ እንዲጠሩ ይደረጋል ። እነሱም ሴቷ ላይ የደረሰውን እያስረዱ ለመብታቸው ይሟገታሉ ። በስተመጨረሻም ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው ባል ይቅርታ ጠይቆ የተፈረደበትን ካሳ ለሚስቱ ከፍሎ ፣ እንደ ማይደግመው ቃል ገብቶ ፣ ህብረተሰቡን አመስግኖ ፣ አብልቶ ፣ የእርቅ ሥርዓቱ ይፈፀማል ። ይህ በኦሮሞ ህዝብ ውስጥ የሚደረግ ከገዳ ሥርዓት ውስጥ አንዱ የሆነው ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት የሚከላከልና የሚቃወም ፣ ቀጥሎም ሴቶች በራሳቸው የራሳቸውን መብት የሚያስከብሩበት መንገድ ነው" ። እኔና የከንቲባው ልጅ ፈዘን ከምንቆም ለምን ሄደን ልጅቷን የተፈጠረውን አንጠይቃትም ብለን ወደሷ አመራን ። ሰላም ብለናት ሁኔታውን ስንጠይቃት "እንደ ምታፈቅረውና እሱ ግን ለሷ ምንም አይነት ስሜት እንደሌለው ፡ የሷ ጭቅጭቅና ተደጋጋሚ የፍቅር ጥያቄ ስልችት ብሎት ካሁን በዋላ አይንሽን ማየት አልፈልግም" ብሏት በጥፊ መቷት እንደሄደ ነገረችን ። 'አይዞሽ በቃ ፡ ይሄም ያልፋል' ብለናት ልንሄድ ስንል ያለችን ነገር አስገረመኝ ። "ኧረ አታስቡ ፡ ከሱ የሚመጣው ማንኛውም ነገር ለኔ ስጦታዬ ነው" ነበር ያለችን ። ለካስ ቴዲ አፍሮ "እያነቡ እስክስታ" ያለው ወዶ አይደለም...✌️
May 12, 2021Harar shewal eid 😍
May 12, 2021Ayii i was going to say hamer too😁 Gn yetemket ken Gondar lay basalef ds ylegnal😍
May 12, 2021Gishen maryam
May 12, 2021