Hi guys ምን መሰላችሁ እኔ የኮሌጅ አስተማሪ ነበርሁ እና የማስተምርበት ኮሌጅ ባለቤት እህቷ ጋር የፍቅር ግንኙነት ነበረን ። የፍቅር ጥያቄው የመጣው በሷ በኩል ቢሆንም በጣም እንፋቀር ነበር። በሀይማኖት ልዩነት አለን ማለቴ እሷ ሙስሊም እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ የሷ ቤተሰቦች የተለያየ እምነት ተከታይ ስለሆኑ በሁሉም ነገር ተግባብተን ነበር። እኔ እሷን በጣም አፈቅራታለሁ እሷም ለኔ ተመሳሳይ ስሜት ነበራት ሆኖም ግን የኔ የሰራ ባልደረባ ታፈቅረኝ ስለነበር ለማለያየት ብዙ ሞክራ በመጨረሻ አለያየችን plus ቤተሰቦቿ በጣም ሀብታም ለሆነ ሰው እሷን መዳር ይፈልጋሉ በዚህ ምክናያት ብዙ ጊዜ ከቤተሰቦቿ ጋር ተጣልታ ታቃለች። ከተጣላን 10 ወር ሆኖኗል እስካሁን መርሳት አልቻልሁም በጣም አፈቅራታለሁ ያለችበትን ሁኔታ ባላቅም አንዳንዴ social media ላይ ሰላምታ እንለዋወጣለን። አሁን የማስተርስ ተማሪ ነኝ ውጭ ለመሄድም ዝግጅት እያደረግሁ ነው ብዙ አድናቂ አለኝ ግን እንደሷ የማፈቅረው ሰው የለም በኑሮየ ላይ ጫና እያሳደረችብኝ ነው ምን ላድርግ ምን ትመክሩኛላችሁ ❓
May 10, 2021Yihe neger ye amarigna film nw ende 😳
May 10, 2021