Hey guys Addis Ababa university any Bachelor Degree lememar kezi befit yechersew Bachelor Degree cost sharing mekfel gedita yenorbnal? Note that the fields might not be relatable.
May 08, 2021አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2013 ዓ.ም. በማታ መርሃግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አመልካቾችን ይጋብዛል በዚህም መሰረት አመልካቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ማቅረብ፤ በዲፕሎማችሁ ወይም ደረጃ 4 ለምታመለክቱ ከትምህርት ማስረጃ ጋር የCOC ደረጃ 4 ማቅረብ ዲፕሎማችሁ የአስተማሪነት ሆኖ ለምታመለክቱ ዲፕሎማ በጨረሳችሁበት የትምህርት አይነት ብቻ በመመዝገብ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ ለPreparatory አመልካቾች ከ2007-2012 ዓ.ም. ድረስ ብቻ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን የምታሟሉ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ¥Qrብ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በተለያየ ምክንያት አቋርጣችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ማሳሰቢያ፡- የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲዉ ድረ ገጽ (https:\\portal.aau.edu.et) መሙላት ከማመልከቻ ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 150 / አንድ መቶ ሃምሳ/ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሞባይል CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም በቅርንጫፍ አማካኝነት በ242424 አጭር ኮድ ክፍያ መፈጸም ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመለከቻ ፎርሙ በመመለስ በፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን የወጪ መጋራት ያጠናቀቁበትን ሰነድ መላክ፤ ምዝገባዉ ካከናወኑ በኋላ የትምህርት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ቢሮ ቁጥር 203 ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡ በዲፕሎማ አመልካቾች የዩኒቨርስቲዉን የመግቢያ ፈተና ጊዜን፤ በዩኒቨርስቲዉ ድረገጽ (www.aau.edu.et) እና (https:\\portal.aau.edu.et) ወደፊት ይገለጻል፡፡ ለአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለማታ የመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች በሙሉ በየትምህርት ክፍሉ ፈተና የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ አውቃችሁ እንድትዘጋጁ እናስታውቃለን፡፡ ለአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለማታ ዲፕሎማ የመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች በሙሉ ከዩኒቨርስቲው መግቢያ ፈተና በተጨማሪም በየትምህርት ክፍሉ ፈተና የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ አውቃችሁ እንድትዘጋጁ እናስታውቃለን፡፡ የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ የመረጣችሁትን ትምህርት ክፍል የምታገኙት 12ኛ ክፍል ጨርሰው እና በዲፕሎማ አመልካቾች ከተመደቡ በኋላ በሚተርፉ ቦታዎች ላይ ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ የምዝገባ ቀን፡ ከግንቦት 02 እስከ ግንቦት 06 2013 ዓ.ም የምዝገባ ቦታ ፡ በሬጅስትራር ህንፃ ቢሮ ቁጥር 203
May 08, 2021