Is there anyone who knows how to register in AAU Commerce, its really urgent for me and i would apperciate any information.
May 07, 2021❇️የምዝገባ ጥሪ በማታ መርሃግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2013 ዓ.ም. በማታ መርሃግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ለመማር የምትፈልጉ ከታች የተገለጸውን መስፈርት በሟሟላት እንድትመዘገቡ ይጋብዛል። 🟣የምዝገባ ቀን: ከግንቦት 02 እስከ ግንቦት 06 2013 ዓ.ም 🟣የምዝገባ ቦታ: ዋናው ግቢ፣ ስድስት ኪሎ በሬጅስትራር ህንፃ ፣ ሁለተኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 203 በዚህም መሰረት አመልካቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል ☘️በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ማቅረብ፤ ☘️በዲፕሎማችሁ ወይም በደረጃ 4 ለምታመለክቱ ከትምህርት ማስረጃ ጋር የCOC ደረጃ 4 ማቅረብ፤ ☘️ዲፕሎማችሁ የአስተማሪነት ሆኖ ለምታመለክቱ ዲፕሎማ በጨረሳችሁበት የትምህርት አይነት ብቻ በመመዝገብ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ፤ ☘️ለPreparatory አመልካቾች ከ2007-2012 ዓ.ም. ድረስ ብቻ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን የምታሟሉ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ፤ ☘️ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በተለያየ ምክንያት አቋርጣችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ፤ Programs available at AAU School of Commerce are the following. 1.BA Accounting and Finance 2.BA Business Administration and Information Systems 3.BA Economics 4.BA Logistics and Supply Chain Management 5.BA Management 6.BA Marketing Management ማሳሰቢያ፡- ✅የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲዉ ድረ ገጽ https://portal.aau.edu.et/ መሙላት ✅ከማመልከቻ ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 150 / አንድ መቶ ሃምሳ/ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሞባይል CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም በቅርንጫፍ አማካኝነት በ242424 አጭር ኮድ ክፍያ መፈጸም ✅ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመለከቻ ፎርሙ በመመለስ በፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን የወጪ መጋራት ያጠናቀቁበትን ሰነድ መላክ፤ ✅ምዝገባዉ ካከናወኑ በኋላ የትምህርት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ቢሮ ቁጥር 203 ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡ ✅በዲፕሎማ አመልካቾች የዩኒቨርስቲዉን የመግቢያ ፈተና ጊዜን፤ በዩኒቨርስቲዉ ድረገጽ (www.aau.edu.et) እና (https:\\portal.aau.edu.et) ወደፊት ይገለጻል፡፡ ✅ለአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለማታ የመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች በሙሉ በየትምህርት ክፍሉ ፈተና የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ አውቃችሁ እንድትዘጋጁ እናስታውቃለን፡፡ ✅ለአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለማታ ዲፕሎማ የመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች በሙሉ ከዩኒቨርስቲው መግቢያ ፈተና በተጨማሪም በየትምህርት ክፍሉ ፈተና የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ አውቃችሁ እንድትዘጋጁ እናስታውቃለን፡፡ ✅የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ✅በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ የመረጣችሁትን ትምህርት ክፍል የምታገኙት 12ኛ ክፍል ጨርሰው እና በዲፕሎማ አመልካቾች ከተመደቡ በኋላ በሚተርፉ ቦታዎች ላይ ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
May 08, 2021