#ሰምና_ወርቅ_001 ቀን ላይ አንድ ጠያቂ ሲያነሳው ትዝ አለኝና እስኪ የእነዚህ ሰዎች የሰምና ወርቅ ብቃት ምን ያህል ነው በማለት 👇🏾👇🏾👇🏾 ፩) ነይልኝ በፈረስ በሚገስግሰዉ! መቸ በቅሎ ያዉቃል እንዳንቺ ያለ ሰዉ ፪) ሞጣ ቀራኒዮ ምነዉ አይታረስ በሬ ሳላይ መጣሁ ከዚያ እስከዚህ ድረሰ ፫) አዉው ብትል ጅቦ መች እፈራሃለሁ ና ብላኝ ና ብላኝ እደጅዋ ቆሜአለሁ ፬) አዳራሹ ሰፊ ቤቱ አልጠበባችሁ በተራ በተራ ምነዉ መግባታችሁ? ፭) ከበጌምድር ጎጃም ተሻገር ያልከኝ ሰሜን ወደሁዋላ ተመልከትልኝ ፮) ለምን ገለበጡት ወተቱን በጋን ችዬ እገፋዋለሁ የማልለዉን ፯) ከዚያ ላይ ያለች፣ሸክላ ሰሪ፣ ድሃ ናት አሉ፣ ጦም አዳሪ፣ ማን ነገራት፣ጥበቡን፣ ገልአፈር መሆኑን። ፰) በጎጃም ያካፋል በሸዋ ፀሀይ በጎንደር ደመና መቅረቱ ነውይ ፱) ቤተስኪያን ስሞ፣ ለመኖር፣ መልካም ነው አሉ፣ ጎንደር፣ አይቀርምና፣መዳኘት፣ ከተማሰው፣ መግባት። ፲)አጼ ዮሐንስ ይዋሻሉ መጠጥ አልጠጣም እያሉ ሲጠጡ አይተናል በእርግጥ ራስ የሚያዞር መጠጥ
14 votes