የኪንታሮት በሽታ(hemorrhoids) ምንነት > በፊንጢጣ ላይ የሚገኙ ደም መላሽ የደም ስሮች ሲያብጡ የሚፈጠር በሽታ ሲሆን በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኝ ቢሆንም በብዛት ከ45 - 65 አመት ባሉት ላይ በብዛት ይከሰታል አይነት(type) ፩. ውጫዊ ኪንታሮት(external hemorrhoids)፦ በላይኛው ቆዳ ላይ የሚገኝ ሲሆን ህመምም አለው ፪. ውስጣዊ ኪንታሮት(internal hemorrhoids)፦ በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ህመም የለውም -> 4 አይነት ደረጃዎች(grade) አሉት። አጋላጭ ነገሮች(risk factors) > አነስተኛ የፍይበር መጠን ያላቸው ምግቦችን ማዘውተር > የሆድ ድርቀት > እርግዝና > የአንጀት ካንሰር > ውፍረት > ሽንት ቤት ሲጠቀሙ ማማጥ > የጉበት በሽታ > ረጅም ጊዜ የቆዬ ተቅማጥ(chronic diarrhea) > በቤተሰብ ያለበት ካለ > እድሜ መጨመር > ኢ-መደበኛ/የፊንጢጣ ወሲብ(anal intercourse) > የህብለ ሰረሰር ጉዳት(spinal cord injury) ምልክቶች(clinical features) > ህመም የሌለው ከፊንጢጣ የሚፈስ ደም > በሰገራ መውጫ አካባቢ ማሳከክ > በፊንጢጣ አካባቢ የህመም ስሜት መኖር > ከፊንጢጣ የወጣ ስጋ መሳይ እባጭ የኪንታሮት ጠንቅ(complications) > የደም መርጋት(thrombosis) > ወጦ አለመመለስ(irreducible) > መመርቀዝ(infection) > ያልተለመደ የሰውነት ክፍተት(fistula) > የሰውነት መሰንጠቅ(fissure) > የደም ማነስ ምርመራ > አካላው ምርመራ > የደም ምርመራ > አኖስኮፒ፣ሲግሞይዶስኮፒ፣ፕሮክቶስኮፒ... ህክምና > የቤት ውስጥ ህክምና ሀ. በፍይበር የበለፀጉ ምግቦችን(አትክልትና ፍራፍሬ..) መመገብ ለ. ፈሳሽ አብዝቶ መውሰድ ሐ. ለብ ባለ ውሃ ጨው ጨምሮ ከ15- 30 ደቂቃ በቀን ሁለቴ/ሦሥቴ መዘፍዘፍ መ. ሁሌም ከተፀዳዱ በኃላ በንጹህ ውሃ መታጠብ ሠ. ለስላሳ የመፀዳጃ ወረቀቶችን መጠቀም > የህመም ማስታገሻ መድኃኒት መጠቀም > የሚቀቡ የኪንታሮት ማጥፊያ መድኃኒት መጠቀም > ቀዶ ጥገና > የጨረር ህክምና ምን እናድርግ? × በፍይበር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ × ማስማጥን ማስወገድ × ሰገራ በሚመጣ ጊዜ ጊዜውን ሳያሳልፉ ወደ ሽንት ቤት መሄድ × በመፀዳጃ ቤት ለረጅም ሰአት አለመቀመጥ × የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ × ቢቻል ከላይ የተጠቀሱ አጋላጭ ነገሮችን ማስወገድ × ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶችን ሲያዩ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ @ethiotena1 @ethiotena1 @ethiotena1
May 07, 2021