Hello guys endet nachu መፅሀፍ ቅዱስ ላይ መሀልየ መሀልየ ዘሰሎሞን yemibal kefl ale aydel? My question is መሀልየ men malet nw?
May 06, 2021ከመዝሙራት ሁሉ የሚበልጥ መዝሙር malt nw
May 06, 2021Hello guys endet nachu መፅሀፍ ቅዱስ ላይ መሀልየ መሀልየ ዘሰሎሞን yemibal kefl ale aydel? My question is መሀልየ men malet nw?
May 06, 2021ከመዝሙራት ሁሉ የሚበልጥ መዝሙር malt nw
May 06, 2021Ok thank you
May 06, 2021በእንተ መሐልየ መሐለይ ዘሰሎሞን ክፍል ፩ እንደሚታወቀው በስቀለተ ክረስቶስ የክረስቶስ አካል የሆነችው ቤተክርስቲያን ተገኝታለች ምክንያቱም ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚነግረን ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ደም ተዋጅታለች እና (ሐዋ ፳፡፳፰) ስለሆነም በሰሙነ ህማማት ቤተክርስቲያን እንድናነበው የምታዘን ይህ መሐልየ መሐልይ ዘሰሎሞን የተባለው ቅዱስ መፅሐፍ ስለሙሽራው ቤተክርስቲያን እና ስለ ራሷ ክርስቶስ የተነገረ ነው እኛ ኦርቶዶክሳውያን በእውነት እንናገራለን። በእውነቱ አለማስተዋል እንጂ መፅሐፍት ሁሉ የሚናገሩት ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ሊቁ ቅዱስ ጀሮም እንዳለው"መፅሐፍትን አለማወቅ ክርስቶስን አለማወቅ ነው" ክርስቶስ ኢየሱስም በአፉ በመዝሙራት በሙሴ ህግ እና በነብያት መፅሐፍት ስለእሱ እንደተፃፈ ነግሮናል። ነገርግን መፅሐፍትን እናስተውል ዘንድ አዕምሮአችንን ካልከፈተልን በፍፁም ልናውቀው አንችልም።(ሉቃ ፳፬፡፵፬-፵፭) ✅መሐልይን ማን ፃፈው? የመሐልይን መፅሐፍ የፃፈው ጠቢቡ ሰሎሞን ነው ለዚህም ማስረጃችን በ፩ነገ፬፡፴፪ ላይ እንዲህ ይላል"እርሱም ሦሥት ሺህ ምሳሌዎችን ተናገረ #መሐልዩም አምስት ሺህ ነበር" ይላል ይህቃል ነብየ እግዚአብሔር ሰሎሞን ምሳሌን ለመፃፉ እና ለመናገሩ እንዲሁም መሐልይን መፃፉን መናገሩን ይነግረናል። ስለሆነም በዚህ ቃል ሰሎሞን መፅሐፉን ለመፃፉ ማረጋገጥ ይቻላል። ✅ስሙ ለምን መዝሙረ መዝሙራት ተባለ? ይህ የሚያመላክተው መዝሙሩ ከመዝሙራት በላይ መሆኑን ነው በእንግሊዝኛውም Song Of Songs ይለዋል። በመፅሐፍ ቅዱስ የጌቶች ጌታ የከንቱዎች ከንቱ...የሚሉ ቃላት እንዳሉ እና እንደምናየው ሁሉ ይህም መፅሐፍ መዝሙረ መዝሙራት መባሉ(የተባለው) ከመዝሙራት ሁሉ ስለሚበልጥ ነው(መሐ ፩፡፩) ✅መፅሐፉ ስለ ስጋዊ ነገሮች ይናገራልን? በዚህ ዘመንም ይሁን ባለፉት ዘመናት መፅሐፉ ስለ ስጋዊ ነገሮች የሚናገር የሚመስላቸው ነበሩ አሉም #ለምሳሌ ረቢ ሻማይ የተባለ በመጀመሪያው ክፍለዘመን የነበረ የአይሁድ ረቢ(መምህር) መፅሐፉን በቀጥተኛው በመተርጎም ከመፅሐፍ ቅዱስ አካልነት እንዲወጣ አድርጎ ነበር [፩] ይሁን እንጂ መፅሐፉን ራሳቸው አይሁዶች ከቀኖና የሚቀበሉት እና የሚገለገሉበት ነው። በጀማኒያ ጉባዔ ቀኖና ላይም ቀንነውታል። በዘመናችንም የሚገኙ ፕሮቴስታንቶች መፅሐፉ ስለ ስጋዊ ሙሽራ እና ሙሽሪት(ፍቅረኛሞች) የተነገረ የተፃፈ እንደሆነ ይናገራሉ።
May 06, 2021✅መፅሐፉ ስለስጋዊ ፍቅረኛሞች አይናገርም። ፩ መፅሐፉን የሚጋሩን አይሁዳውያን ለራሱ የተረዱት እና የሚተርጉሙት እንደዚህ ነው በመንፈስ ቅዱስ የተነገረ እንዲሁም እግዚአብሔር እኛን የሚያወድስበት እኛም እግዚአብሔርን የምናወድስበት(በነፍስ እና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን አንድነት) የሚያሳይ ነው ብለው ነው የሚረዱት።[፪] ፪ጥንታውያን ክርስቲያን ሊቃውንት አባቶቻችን መፅሐፉን በስጋዊ መንገድ አልረጎሙትም(አልተረዱትም) ለምሳሌ ሊቁ ኦሪገን፣ቅዱስ ጀሮም፣ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ፣ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ሊቁ አውግስጢኖስ... እና ሌሎችም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ይህ መፅሐፍ ስለ ክርስቶስ እና ስለቤተክርስቲያን እንዲሁም በክርስቲያን ነፍስ እና በክርስቶስ መካከል ስላለው ግንኙነት[፫] ያስረዳል ብለው ነው የተረጎሙት። አባቶችም ይህን መፅሐፍ የምስጢራት መፅሐፍ፣የአዋቂ መፅሐፍ፣የሰማያዊ ሰርግ መፅሐፍ...እያሉ ይጠሩታል ስለዚህ ክርስቲያን ነን እና ማንን እንከተል? ✅መፅሐፉ እኮ ስለስጋዊ ሙሽራዎች(ፍቅረኛሞች) ነው የሚናገረው? ፩ መፅሐፉ ራሱ እንደዚህ ዓይነት አረዳድ እንዳንረዳ በሩን ይዘጋብናል። #ለምሳሌ መሐ፩፡፫ ላይ እንዲህ ይላል "ዘይትህ መልካም መዓዛ አለው ስምህ እንደሚፈስ ዘይት ነው ስለዚህ ደናግል ወደዱህ" እዚህጋ ሙሽራይቱ ስለሙሽራዋ ማንነት ስለስሙ ውበት ገልፃለች ከዚያም ደናግል እንደወደዱት ገልፃለች እንዴት ብሎ ነው ሌሎች ደናግሎች ሙሽራዋን በወደዱት ጊዜ የምትደሰተው? ስለዚህ ይህ ቃል ስለ ስጋዊ ሙሽራዎች እንዳልተነገረ እናረጋግጣለን።[፬] ፪ በሰው እና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን አንድነት ግኑኝነት ለመግለፅ እንደ መሐልይ መፅሐፍ ዓይነት የጋብቻ ምሳሌዎች በሌሎች የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ስለተገለጡ(ኤር ፪፡፪ ሕዝ ፲፮፡፩-፲፬ ሆሴ፪፡፬) [፭] እነዚህ ቃላት በዘመነ ብሉይ በነበሩት በእስራኤል ዘስጋ እና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን አንድነት እና ቃልኪዳን በባል እና በሚስት መስለው የሚናገሩ ሲሆን የመሐልይን መፅሐፍ ምሳሌዎችን በዚሁ መረዳት እንችላለን። ✅መፅሐፉን በስጋ ዓይን ለሚያነቡ ሰዎች ምክር ሊቁ ኦሪገን እንዳለው "ለስጋዊ ሰዎች ይህ መፅሐፍ አደገኛ ነው...በስጋዊ ጨለማ ያሉት ይህን መፅሐፍ አያንብቡ" [፮] እኔም እላለሁ "ፊደል ይገድላል መንፈስ ግን ህይወትን ይሰጣል" እንዳለ ብርሃነ ዓለም ጳውሎስ (፪ቆሮ ፫፡፮) መፅሐፉን ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እንዳለው በመንፈሳዊ ዓይን እና አስተሳሰብ አንብቡት ብለን እንመክራለን። ✅ማጠቃለያ ብርሃነ ዓለም ጳውሎስ በኤፌ ፭፡፴፪ ላይ የዘፍ ፪፡፳፬ን ለአዳም እና ለሔዋን የተነገረውን ቃል ለቤተክርስቲያን እና ለሙሽራዋ ክርስቶስ እንደሚተረጎም ነግሮናል። ስለዚህ እኛም የሐዋርዬትን ፈለግ ተከትለው የተነሱ አባቶች ያውም መፅሐፉ ስለስጋዊ ነገር የማይነናገረውን ስለቤተክርስቲያን እና ስለ ሙሽራዋ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ብለው ሲናገሩ ፣ሲያስተምሩ እና ሲተረጉሙ ይህን ክርስቲያናዊ አተረጓጎም ከማን ወስደውት ነው ከአባታቸው ከብርሃነ ዓለም ጳውሎስ አይደለምን? እኛ ነው ብለን እንመልሳለን። ✅ማጣቀሻወች ፩ F.r tadros y.malaty, song of songs page 5 ፪ F.r tadros y.malaty, song of songs page 5 & 7 ፫ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሱስ የመሐልይን መፅሐፍ የተረጎመው በክርስቶስ ኢየሱስ እና በክርስቲያን ነፍስ መካከል በአለው ግንኙነት ነው። ፬ F.r tadros y. malaty, song of song page 7 ፭ F.r tadros y. malaty, song of songs page 12 ፮ F r tadros y. malaty, song of songs, page 11 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ጌታ እግዚአብሔር መንፈሳዊ ዓይን ይስጠን አሜን ይቀጥላል... @APOSTOLICsuccession
May 06, 2021ከመዝሙር ሁሉ የሚበልጥ የሰለሞን መዝሙር ማለት ነው ...✌
May 07, 2021ከመዝሙር የሚበልጥ መዝሙር ማለት ነው። "መኃልይ" ተብሎ ነው የሚጻፈው
May 07, 2021ከምስጋናዎች ሁሉ የሚበልጥ የሰለሞን ምስጋና
May 06, 2021Mehalye= "Yemehal yemehalun" malet new literally
May 06, 2021