IT'S URGENT ‼️‼️ Betam kebad ras metat yzognal gemashun new miyaumegn aynen chemro(i think it's migraine) ena ebakachu mefthe kawekachu🙏🙏
May 04, 2021#ማይግሬን(#Migraine #Headache) 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ 👉👉 ዉድ የዶክተር አለ ተከታታዮች ማይግሬን ከፍተኛ እና በተደጋጋሚ ግማሽ ከፈሎ የሚከሰት ራስ ምታት ነው።ጭንቅላት ዉስጥ የሚገኙ የደም ስሮች እብጠት መኖር በዙሪያቸው ከሚገኙ ነርቮች የተለያዩ ንጥረ ነገሮች እንዲለቁቀ ያደርጋል፡፡ የተመረቱ ንጥረ ነገሮች አእምሮአችን ለህመም ያለውን ስሜት ከፍ ያደርጉታል እና ከፍተኛ የራስ ምታት ያስከትላል፡፡ህመሙ ከአራት ሰአት እስከ ሁለት እና ሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከጭንቅላት እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ይባባሳል፡፡ 👉👉 #ለማይግሬን #አጋላጭ #ሁኔታዎች 📌 በፆታ ሴት መሆን 📌 እድሜ ከ10-40 📌 በቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር ካለ 📌 ጭንቀት/ድብርት 📌 የእንቅልፍ ችግር 📌 የሚጥል በሽታ #የማይግሬን #ምልክቶች 📌 ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ 📌 ከፍተኛ የድካም ስሜት 📌 ብርሐን፣ ድምፅ እና ሽታ መጥላት 📌 የምግብ ፍላጎት ማጣት 📌 ዉሃ መጠማት/የከንፈር መድረቅ 📌 የሆድ መነፋት 📌 የስሜት መዋዠቅ 📌 ድርቀት ወይም ተቅማጥ 📌 ቅዠት(የሌለ ብርሐን፣ ጥቋቁር ነጠብጣብ መታየት) 📌 ጣዕም እና ሽታ ለመለየት መቸገር 📌 የእይታ መደብዘዝ 📌 በግማሽ በኩል የሰዉነት መዛል/አለመታዘዝ 📌 እግር እና እጅ ላይ የመክበድ ስሜት/መደንዘዝ 📌 ጆሮ ላይ የደዉል ድምጽ መሰማት #ማይግሬንን #የሚያባብሱ #ሁኔታዎች 📌 የሆርሞን መለዋወጥ 📌 ጭንቀት 📌 ምግብ አለመብላት/ርሀብ 📌 የአየር ንብረት መቀያየር 📌 ምግቦች እንደ አይብ፣አልኮል፣ቸኮሌት፣ኮምጣጣ ምግቦች 📌 የደም ቱቦ የሚለጥጡ መድሐኒቶች 📌 የእንቅልፍ መዛባት #የማይግሬን #ህክምና 📌 የህመም ማስታገሻ መድሓኒት፣ ቫይታሚን ቢ መዉሰድ 📌 ጨለማ እና ፀጥ ያለ ክፍል ዉስጥ በቂ እረፍት ማድረግ 📌 በቂ ዉሃ መጠጣት 📌 የዝንጅብል ሻይ ፣አፕል እንዲሁም በማግኒዥየም የበለፀጉ ምግቦች መመገብ 📌 ፎጣ በቀዝቃዛ ዉሃ ነክሮ ወይም በረዶ ጭንቅላት ላይ ማድረግ 📌 ጭንቅላት እና የእጅ መዳፍን ማሸት 📌 ቋሚ የሆነ ሰዉነትን የማሳሳብ እንቅስቃሴ እና አርማሞ መስራት ችግሩ እንዳይከሰት ያደርጋል 👉👉 በማንኛውም ከጤና ጋር ከተያያዙ ችግሮች ላይ ለመመካከር ካስፈለገዎት 8809 ላይ ይደውሉ! ከጧት 2 ሰዓት እስከ ማታ 1 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!!
May 05, 2021