የአገራችንን ገጽታ ለመቀየር በሚደረገው ሂደት ውስጥ ትምህርት ወጣቱ የነገ አገር ተረካቢ ስለሆነ በተሻለ እውቀትና ችሎታ ተገንብቶ እንዲወጣ ጉልህ ሚና ይጫወታል።ስለዚህ ካሁን በፊት የነበረውም ሆነ አሁን ያለ የትምህርት ሂደት ይህንን ዓላማ አሳክቷል ልንል እንችላለን?
May 02, 2021#10 ሰዓት ላይ class ነበረኝና በፍጥነት ቁና ቁና እየተነፈስኩ ክፍላችን ደረስኩኝ ። #20 ደቂቃ አርፍጃለው ። ሆኖም ግን አስተማሪው ተንበርከክ ሳይለኝ አስገባኝ ። የ machine element መምህራችን ህንዳዊ ዜጋ ነው ። ያው የሱ ትምህርት ትርጉም በስለሺ እስኪመጣልን ድረስ ምንም እየገባን አይደለም ። ድንጋዩ ማነው እንዳትሉኝ እንጂ ድንጋይ ላይ ውሃ እያፈሰሰ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም ። ሰውዬው ከሚያወራቸው ነገሮች አንዲት እንኳን አትሰማም ። ከሱ እንግሊዝኛ ይልቅ የ shah rhuk khan ህንደኛ በስንት ጣዕሙ ። ደግሞ መቸክቸክ አይደክመውም ። አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አምስት ጊዜ black board እያጠፋ እየፃፈ ፡ እኛንም ያለ ሞያችን ደራሲ አርጎናል ። እኔ ለሰባቱም ትምህርቶች ትበቃለች ብዬ የገዛዋትን አንዷን ባለ #50 ወረቀት ደብተር እሱ በአንደኛው ቀኑ ነበር ብቻውን መሃል ላይ ያደረሳት ። anyways ግን ከህንድ የሚመጡት አስተማሪዎች ይሄን ሁሉ km አቋርጠው የሚመጡበት ምክንያት አይገባኝም ። ሀገር ውስጥ አስተማሪ ጠፍቶ ነው እንዳንል ስንቱ ተመርቆ ስራ ጠፍቶ እቤት ውስጥ ተጎልቷል ። የማስተማር ብቃት ፈልገውም ከሆነ የኛዎቹን የሚበልጡበት አንድም የተለየ ብቃታቸው አይታየኝም ። እንግሊዝኛቸው ግራ የሆነ ። ከኛ ጋር መማር ማስተማሩ ላይ በቋንቋ ካልተግባባን ምኑን ተማርን ። በቋንቋም ብንግባባ ደግሞ የትምህርት አሰጣታቸው የህፃን ጨዋታ ነው ። ሰሌዳው ላይ የሀገር Note ይፅፉና እሱኑ መልሰው ያነቡልናል ። አለቀ ፡ ደቀቀ ። እኛ ማንበብ ከብዶን ነው እንዴ የመጣነው ...? ✌️
May 03, 2021