❓❓❓❓❗️❗️❗️👇 ትምህርት ያቋረጥኩት ከ9ኛ ክፍል ነው ለረጅም ጊዜ ስደት ላይ ቆይቼ ወደ ሀገር ልገባ ነው ።እና ያቋረጥኩት ትምህርት ልቀጥል አስቤ አሁን የ9ኛ ተማሪዎች ፈልፈላ ናቸው ሼም ያዘኝ ከነሱ ጋር ቁጭ ብሎ መማር ።የማታ እንዳልማር እኔ ያለሁበት አካባቢ ማታ ለሴት ልጅ ያስፈራል። አንዱ ልቤ ደሞ ትምህርቱ ቀርቶ ቱርክ እየተመላለሽ ንግድ ጀምሪ ይለኛል። ምን ይሻላል ይሄን የምታነቡ በሙሉ ያላቹን አስተያየት ላኩልኝ🙏
Apr 23, 2021እንዲህ በማለት እራስሽን አትግደይ። ሃገራችን ውስጥ ብዙ እድሜያቸው በጣም ገፍተው የተማሩ ብዙ ስኬታማ ሰዎች አሉ። አንቺን እንደማየው ደሞ እድሜሽ እስከዚም ገፋ የሚባል ዓይነት አይደለም፥ አብዛኛው የሃገራችን ክፍል በዚው ስላሉ ማለቴ ነው። ዛሬ እንደነ ሰዓሊው ዶ/ር ለማ ጉያ ያሉ ሰዎች 1ኛ ክፍልን በ15 ዓመታቸው ገብተው እድሜያቸውን ሳይሆን ዓላማቸውን ገፍተው የተማሩ ስኬታማ ሰዎች አሉ። እነሱን እንተው፥ እኔ ከማውቀው በ39 ዓመቱ 1ኛ ክፍል ገብቶ ማስተርሱን የጨረሰ ሰው አለ። "እንዴት ሊሆን ቻለ ካልሺኝ"? ብሩህ ዓላማ ስላለው። So, እንቺ ለመማር የሚያስፈልግሽ እድሜሽ ሳይሆን ዓላማ ነው። ዓላማ ካለሽ ተማሪ! የማይማረው ዓላማ የሌለው ብቻ ነው። ከሁሉም በላይ ግን ዓላማሽን ለማደናቀፍ ብዙ መሰናክሎች ስለሚኖሩ፤ በራስሽ ተስፋ አትቊረጪ። ከሁሉም በላይ እግዚአብሔር በሰላም ወደ ሀገርሽ ያግባሽ😊
Apr 23, 2021