እኛ ኢትዮጵያዊያን ከእርስ በርስ ጦርነት ቅርብ ርቀት ላይ የምንገኝ አይመስላችሁም? አውዳሚዎቹ የኦሮሞ ብሄርተኞች ታላቋን የኦሮሚያ ሪፐብሊክ በመመስረት ሂደት ተጠምደው ህዝብ ይፈጃሉ። የአማራ ብሄርተኞች ለህዝባቸው "እኛ ብቻ ነን ያለንልህ፤ አማራ ተነስ!" እያሉ ንፁህ ኢትዮጵያዊ የሆነውን ህዝብ እየመረዙ ብሄርተኛ እንዲሆንና በጥላቻ እንዲጠመቅ ይገፋፋሉ። የትግራይ ብሄርተኞች በግትርነትና የስልጣን ሀራራ ያጡትን ስልጣን ለማስመለስ ኢትዮጵያ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ከባድ ጫና እንዲደርስባት እያደረጉ ይገኛሉ። አብዛኛው ህዝብ ደግሞ ዝምታን መርጧል። እናም መጨረሻችን ምን ይመስላችኋል? ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአፋቸው እንደሚሰብኩት እውነት ኢትዮጵያ አትፈርስም? ለዚህ ሁሉስ ማንን ነው ተጠያቂ የምናደርገው?
Apr 19, 2021ለጥያቄው እና ላጡያየቅሽ/ህ ብቻ ራሱ ጭብጨባ ያስፈልጋል። አብዛኛው የማያቸው ጥያቄዎች የሆነ ወገንን ከሚደግፉ ሰዎች የሚመጣ ነው፣ የእውነተኛ ኢትዬጽያዊ ጥያቄ እግዴ ይሄን ይመስላል ጎበዝ!
Apr 19, 2021