ሰላም ሰላም ስለ ጳውሎስ ኞኞ የሚያትት ነገር ካላችሁ,,pls
Apr 16, 2021ጳ ው ሎ ስ ኞ ኞ (1926 - 1984) ----------------------- ጳውሎስ ኞኞ ከእናቱ ከወይዘሮ ትበልጫለሽ አንዳርጌና ከግሪካዊ አባቱ ሚስተር ኞኞ ህዳር 11 ቀን 1926 ዓ.ም. በቁልቢ ከተማ ተወለደ። ትውልዱ ቁልቢ ይሁን እንጂ የልጅነት ጊዜውን ያሳለፈው በድሬዳዋ ነው። እድሜው አስር ዓመት ገደማ ሲሆነው ድሬዳዋ ከተማ በሚገኘው ክርስቶስ ትምህርት ቤት ገብቶ የቀለም ትምህርቱን ጀመረ። በትምህርት አቀባበሉ ፈጣን ስለነበር 'ደብል' እየመታ በአጭር ጊዜ ወደ አራተኛ ክፍል አለፈ። ነገር ግን ትምህርቱን ከዚህ በላይ መቀጠል አልቻለም። ወላጅ እናቱ ምንም ገቢ ስላልነበራቸው ገና በመማሪያ እድሜው እናቱን ለመርዳት ደፋ ቀና ማለት ጀመረ። ስዕል በመጠጥ ቤቶች አዙሮ በመሸጥ ራሱንና ደሀ እናቱን ያስተዳድር ነበር። ጳውሎስ ኞኞ በ1943 ዓ.ም. ገደማ ገና የ17 ዓመት ታዳጊ ወጣት ሳለ በእርሻ ሚኒስቴር ተቀጠረ። በሚኒስቴሩ የእንስሳት ህክምና ክፍል የእንስሳት መርፌ ወጊ ሆኖ በወር ስምንት ብር እየተከፈለው በጊዜው አጠራር ሀረርጌ ክፍለ ሀገር ጨርጨር አውራጃ ለሶስት ዓመታት ሰርቷል። በ1946 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል በሰማንያ ብር ወርሀዊ ደመወዝ በድሬሰርነት፣ በፀሀፊነትና በሂሳብ ስራ አገልግሏል።
Apr 16, 2021