Hey Guys, I'm suffering from acne since i was 14 and i am still struggling at the age of 27 so could you please suggest me any good dermatologist or home remedies medicine to cure acne? Thanks.
Apr 02, 2021ብጉር(acne vulgaris) ምንነት > የተለመደና አብዛኞቻችንን የሚያጠቃ የቆዳ ችግር ሲሆን የሚከሰተውም በቆዳችን የሚመነጭ ቅባት ወይም የሞቱ ሴሎች የቆዳ መውጫ ቀዳዳዎችን ሲደፍኑ ነው። አጋላጭ ምክንያቶች > የሰውነታችን ቅመሞች(hormones) መለዋወጥ(በተለይም በጉርምስና እድሜ ክልል) > ሆርሞኖችን የያዙ መድኃኒቶች > ቅባትነት ያላቸውን መዋቢያዎችን መጠቀም > ጭንቀት > የወር አበባ መምጣት > በቤተሰብ ውስጥ ብጉር ካለ(genetic) ምልክቶች- እንደ አይነቶቻቸው ይለያያሉ - ነጭ የሆኑ ብጉሮች(ቀዳዳዎቻቸው የተደፈኑ) - ጥቁር ብጉሮች(ቀዳዳዎቻቸው ክፍት የሆኑ) - ቁስለት ያለው ብጉር - መግል የያዙ ብጉሮች(የባክቴሪያ ኢንፌክሽን ያለው ብጉር) - ጠጣር ብጉሮች(ትልቅና ህመም ያለው ብጉር) ህክምና > የሚቀቡ መድኃኒቶች(retinoid) > እንክብል መድኃኒቶች > የሆርሞን ህክምና > ጨረር(PDT) > ቀዶ ህክምና(intralesional steroid,comedon removal) > ምግብን ማስተካከል ምን እናድርግ? × ብጉር የወጣበትን ቦታ በስሱ ማፅዳት- በውሃና በሳሙና በቀን ሁለቴ መታጠብ × ቅባታማ የሆኑ የመዋቢያ ውጤቶችን አለመጠቀም × በብጉር የተጎዳን ቆዳ በእጅ አለመነካካት × ከባድ የጉልበት ስራ ከሰሩ በኃላ እንዲሁም ከፍተኛ ላበት በሚኖር ጊዜ ገላዎን በሳሙና መታጠብ × ጭንቀትን ማስወገድ × ጣፍጭ ነገር አብዝተው አለመመገብ በአንፃሩ በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ
Apr 02, 2021