Sleam sewoch sle history tarik miyak kale King ሱሲንዮስ ye ካቶሊክ እምነት tktay yhonbt mknyat mndn nbr ,?
Mar 31, 2021ከሱስንዮስ 6 ትውልድ በፊት አንድ ሮማዊ (ካቶሊክ) ቄስ በዛ ዘመን የነበረውን ንጉሥ (ስሙን አላስታውሰውም) ትክክለኛው የመሠረተ ሀይማኖት ትምህርት የሮማው እንጂ የእስክንድርያው (ግብፁ) እንዳልሆነ ያስረዳዋል። እናም ሃገሪቱን ካቶሊካዊት ማድረግ እና በፖፑ ሥር እንዲገዙ እንደሚፈልጉ ሲያሰርዷቸው አጼውም አባቶችን ላምክር ብሎ 2 መነኮሳትን አማከረ። እነሱም "ጉባኤ ይካሄድ እና ክርክሩን የረታው ይምራን" አሉ ጉባኤም ተደረገ። ካቶሎክን ወክለው በርካታ ሮማውያን፤ ተዋሕዶን (እስክንድሪያን) ወክለው በርካታ ኢትዮጵያውያን ተቀመጡ። ኢትዮጵያውያንም አሳምነው ረቱ። እናም ወደ ሮማ እንዲመለሱ ውሳኔ ሊተላለፍ ሲል ንጉሡ ለቤተ መንግሥት ሥራ ስለሚፈልጋቸው እንዲቀለብሱ ይለምናል። ከዛም ጉባኤውን የመሩት ባሕታዊው ተነስተው እንዲ አሉ "እነዚ ሰዎች እዚ ከቀሩ እንዲ ይሆናል። ይህንን አስተምህሮ ሸሽገው ለልጆቻቸው ያስተላልፋሉ፥ በ6ተኛውም ትውልድ እነሆ ንጉሡ ከወረማዊያን(ወረሞ) ሃገር ሂዶ ከነሱ ጋር ተዋግተው ተሸንፎ ይማረካል። ከነሱ ዘንዳም ጥቂት ቆይቶ በነሱ እገዛ ወደ መንበሩ ይመለሳል። ሲመለስም በነዚ ሰዎች ልጆች ተታሎ የነሱ የሮማውያንን ትምህርት ይቀበላል" አሉ። እናም እንደ ተባለው ተማርኮ፣ በዛው ከኖረና ለሚስት ካጋቡት በኋላ ወደ ሥልጣኑ ሲመለስ ሜንዴዝ የሚባል ሰው(ቄስ) አስኮተለከው......ከዛ እነዛ ነገሮች ሁሉ ተፈጸመ። አጼ ፋሲል ነግሦ ሜንዴዝን ወደ ኤርትራ ካባረረው በኋላ ፀጋ እና ቅባት የሚባል እንክርዳድ በቤተክርስቲያኒቱ ዘርቶ እንደወጣ በኩራት ተናገረ።
Mar 31, 2021