Aresawem milewen Ye ortodox mezmur lakulegn
Mar 29, 2021#አልረሳውም_ያንን_ዕለት አልረሳውም ያንን ዕለት አልዘነጋው ያን ደግነት እናቴ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት እምዬ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት ስላለኝ ነው ምክንያት/፪/ ለሠው ተናግሬ ያልተረዳኝ ሰው ዕንባዬ በምሬት ከዓይኔ የሚፈሰው የቤቴን ገመና ሁሉን ስነግርሽ አዛኝት ነሽና እራራልኝ ልብሽ አረሳው መቼም የአንቺን ደግነት/፪/ ውለታ አለብኝ ኪዳነ ምሕረት #አዝ ልቤ በሐዘን ጠቁሮ ውስጤ እየደማ መቅረዜ ሲጨልም ስዋጥ በጨለማ በራፌን ዘግቼ ዝም ብዬ አለቅሳለሁ ግን እኔ አቀርቅሬ እናቴ እልሻለሁ ዘንበል አልሽልኝ ሠምተሽ ፆሎቴን/፪/ አልተጸየፍሽም ብቸኝነቴን #አዝ እናት የለኝ ብዬ ከቶም አልከፋ እኔስ አይቻለሁ ስትሞይኝ በተስፋ ምድራዊዋ እናቴ ለጊዜው ነው ፍቅሯ ያንቺስ ግን ልዩ ነው ኧረ ስንቱን ላውራ ማርያም ማርያም ብል አልሠለችሽ/፪/ በልቤ ጽላት ስለ ታተምሽ #አዝ ሲረበኝ መጥተሻል ሲጠማኝ ደርሰሻል ለጎደለው ቤቴ በረከት ሆነሻል ጭንቄም ቀለለልኝ ሐዘኔም ራቀ ያስጨነቀኝ ጠላት ራሱ ተጨነቀ መዳኒት ወልደሽ ዳንኩኝ ከህመሜ/፪/ ይኸው ዘመርኩኝ በምልጃሽ ቆሜ #ሼር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mar 30, 2021