How to love someone?
Mar 21, 2021የሆነ ነገሯ ይማርከዋል ፡ #90% መልኳ ፣ አካሄድ ፣ አለባበስ ፣ አነጋገር ፣ ወዘተ ። ይተዋወቃሉ ፡ ከጥቂት ቀናት በዋላ ፡ ካላገኘዋት ፣ የኔ ካልሆነች ፣ ህይወቴ ካለሷ ባዶ ነው ፣ ወዘተ ማለት ይጀምራል ። አነዚህን ነገሮች እያለ ያለው ለልጅቷ አስቦ አይደለም ፡ ለራሱ ፍላጎት እንጂ ። ደስ ስላለችው ፣ ስለምታምር ፣ ትሆነኛለች ብሎ እንጂ ለልጅቷ እሆናታለው ፣ ብሎ አይደለም ። መጀመሪያ ላይ አፈቀርኳት ብሎ ሲያወራ የሱ ህይወት ካለሷ ባዶ ሆኖ ስለተሰማው እንጂ የሷ ህይወት አሳስቦት አይደለም ። የሱ ጭንቀት እንጂ የሷ ፍላጎት አልታየውም ፤ አያውቅምም ። በቃ በዛ ሰዓት እሱ የሚፈልገው ነገር ቢኖር ልጅቷ የሱ እንድትሆን ነው ። እሷ እንኳን የሌላ ሰው ሆና ማየቱ ይቅርና ሰላም እንኳን ቢሏት ካልገደልኳቸው ሊልም ይችላል ። እሷን ከራሱ ውጪ ከሌላ ሰው ጋር ለሴኮንድ እንኳን ማሰብ አይፈልግም ። እሷ አልፈልግህም ብትለው እንኳን በግድ ካልሆንሽ የሚል ጉድ ውስጥም ሊገባ ይችላል ። ይሄን ሁሉ እያደረገ ያለው ለራሱ ሲል ነው ። ይሄንን ነው እንግዲህ ፍቅር ብለን የጠራነው ። ግን ከዚህ ሰው በላይ እራስ ወዳድ ሰው በምድር ላይ የለም ። ፍቅር ከራስ አልፎ ለሰዎች ሁሉ መኖርና መሞት ነው ። በአይኑ ሳይሆን በልቡ ማየት ሲጀምር እሱ ሳይፈልገው ቤቱ ድረስ መጥቶለት ደጁን ያንኳኳል ። አፍቃሪ መሆን ከፈለገ ከልቧ ውጪ ምኗንም ሳያይ ይውደድ ። ለጎዶሎው ብሎ ካፈቀረ አንድ ቀን እንዳልተሟላለት አስቦ ሊተዋት ይችላል ። ፍቅር መጠቀም ሳይሆን መጥቀም ነው ። እውነተኛ አፍቃሪ በነገሮች ሁሉ ቅድምያ ለራሱ ሳይሆን ለሌላ ሰው ሰጥቶ የሚጠቅም እንጂ የራሱን ችግር ለማሸነፍ ብሎ በሌሎች የሚጠቀም አይደለም'...✌️
Mar 21, 2021