Selam sewoch Zare leteykachu yemfelfew yehonech lij alech ahun gwadegaye nat endemqedatm negryat ene alfelgm blagalech enem beka eswan be weste eyafekerku friendship eyeketelku new yalehut ena ahun sesema àhun chrush endalat kelela sew sesema tenadedku ena mn larg?
Mar 20, 2021ፍቅር ከራስ አልፎ ለሰዎች ሁሉ መኖርና መሞት ነው ። ቢተያዩም ባይተያዩም ፣ ብታምርም ባታምርም ፣ ለሱ ህይወት አስፈላጊ ሆነች አልሆነች ፣ እውነተኛ ልብ ካለው ያኔ የእውነት ፍቅር ከልቡ ይገባል ። በአይኑ ሳይሆን በልቡ ማየት ሲጀምር እሱ ሳይፈልገው ቤቱ ድረስ መጥቶለት ደጁን ያንኳኳል ። አፍቃሪ መሆን ከፈለገ ከልቧ ውጪ ምኗንም ሳያይ ፣ ምንም ሳታደርግለት ፣ ብትበድለው ብትክሰው ፣ ለሱ ሆነች አልሆነች ፣ ባጠቃላይ የሷ ነገር አሳስቦት እንጂ የሱ ጎዶሎነት ተሰምቶት አይውደድ ። ለጎዶሎው ብሎ ካፈቀረ አንድ ቀን እንዳልተሟላለት አስቦ ሊተዋት ይችላል ። የሷን ጎዶሎ ሊሞላ ቢሯሯጥ ግን አትራፊ ይሆናል ። ቅዱሱ መፅሐፍም "ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው" አይደል የሚለው ። ክርስቶስስ ከሰማይ ላይ ወርዶ የሰውን ስጋ የለበሰው ለራሱ ጥቅም ይመስልሻል ...? ፍቅር መጠቀም ሳይሆን መጥቀም ነው ። እውነተኛ አፍቃሪ በነገሮች ሁሉ ቅድምያ ለራሱ ሳይሆን ለሌላ ሰው ሰጥቶ የሚጠቅም እንጂ የራሱን ችግር ለማሸነፍ ብሎ በሌሎች የሚጠቀም አይደለም' ።
Mar 20, 2021