ወደ ዛሬ ጥያቄዬ ስገባ እስከ ዛሬ ተመልካች ብቻ የነበራችሁ ዛሬ እንድትሳተፉ እና የእስከ ዛሬ ተሳታፊዎች ደሞ ተሳትፎ ይቀጥል😇😇 ጥያቄ : - በመፅሐፍ ቅዱስ ወይም በቅዱስ ቁርአን ላይ መላዕክት ቀይ ናቸው ሰይጣን ደሞ ጥቁር ነው የሚል አለ? ወይስ ሰአሊው በምናቡ የሳለው ነገር ነው ነጭ ወይም ጥቁር ሚያረገው ምክንያቱም ሰይጣን በፊት መልዐክ ስለነበር ወይስ ደሞ ፈረንጆች እንደሚሉት ለ ጥቁሮች ያላቸውን ጥላቻ ለማሳየት ጥቁሮች ሰይጣን እራሳቸውን ደሞ ነጭ መላዕክት አርጎ ለማሳየት ያረጉት ነገር ነው እና ደሞ ኢንግላንድ angel land ከሚል የመጣ ነው ስለሚሉ Angel land (የ መላእክት ቦታ) እና እራሳቸውን የመልዕክት ዘር ነን ስለሚሉ የ እነሱ ተፅዕኖ ነው እኛ መላዕክትን ነጭ አርገን በምናብ እንድንስል ያረገን ነገር?? ወይስ??
Mar 15, 2021እንደ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን፤ መፀሀፍ ቅዱስ ስለ ሰይጣን ጥቁረት አይናገርም “ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና።” — 2ኛ ቆሮ 11፥14 ከዚህ ቃል እንደምንረዳው ሰይጣን ምንም እንኳ ከክብሩ ጎድሎ ወደ ጥልቁ ቢጣልም የሰው ልጆችን ለማሳት ብርሃናውያን መላዕክትን እስከመምሰል መለወጥ እንደሚችል ነው። እናታችን ሄዋንንም በእባብ አድሮ አስቷታል ዳግመኛም ከአዳም ጋር ከያዙት ሱባኤ በመልዐክ ተመስሎ አቋርጧቸዋል። በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥንታዊ ስነ-ስዕል ላይ ሰይጣን በግራጫ ቀለም ይወከላል በተለያዩ የአለም አብያተ ክርስቲያናትም እንዲሁ በግራጫና ጥቁር ቀለም ይወከላል ይህ ጥቁር ቀለም የጨለማ ምሳሌ ከመሆኑ ጋር የተገናኘ እንጂ ከጥላቻ የመነጨ አይመስለኝም አሁን አሁን በ እኛ ቤተክርስቲያንም ጥቁር ተደርጎ ይሳላል ይህ ማለት ግን ሰይጣን ጥቁር ነው ማለት አይደለም። ምናልባት በ colonization ጊዜ የነበሩ missionary ዎች ለእኩይ ምግባር ተጠቅመውበት ይሆናል እንጂ ቤተክርስቲያን ጥላቻን አትሰብክም። ሰይጣንም ቀለም የለውም መላዕክትም ብርሀናውያን ናቸው😊
Mar 15, 2021