ShEger wust arif sira indet magignet yichalal...with Out Degree?.. yemitakutin tekumugn.
Mar 15, 2021ከአንድ አመት በላይ ያለምንም ስራ የተቀመጡት ሃኪሞች ፦ በአማራ ክልል 400 በላይ (ቁጥሩ ከዚህም ከፍ ሊል ይችላል) የህክምና ትምህርታቸውን ተከታትለው ያለስራ የተቀመጡ ሃኪሞች/ዶክተሮች/ ለከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና እየተዳረጉ ይገኛሉ። ወደስራ መሰማራት ሳይችሉ ከቀሩ ሃኪሞች መካከል የቲክቫህ አባላት የሆኑም ይገኙበታል። ሃኪሞቹ ከአንድ አመት በላይ ለሚሆን ጊዜ ያለስራ የተቀመጡ ሲሆን ለሚመለከታቸውን የመንግስት አካላት አቤት ቢሉም የተሰጣቸው መልስ "በጀት የለንም" የሚል እንደሆነ ተናግረዋል። በሌሎች ክልሎች እንዳይሰሩም የቋንቋ ጉዳይ ፈተና እንደሆነባቸው ገልፀዋል። የሃኪሞቹ ጥያቄ ዛሬም ድረስ ባይቋረጥም መፍትሄ አልተገኘም ፤ በዚህም ለከፍተኛ የስነልቦና ጫና ተዳርገዋል። ከነሱ አልፎም ቤተሰቦቻቸውን ለስነ ልቦና ጫና ዳርጓል። በሀገራችን የህክምና ትምህርት የሚከታተሉ ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ፣ ከታች ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ለቀለም ትምህርት ብቻ ቦታ እየሰጡ የመጡ፤ ዩኒቨርሲቲ ከተገባ በኃላም ከባድ 7 ዓመታትን አልፈው ነው የሚመረቁት። ሃኪሞቹ ለበርካታት አመታት ያህል በስንት ጥረት እና ትግል እዚህ ደርሰው ከፍተኛ የሃኪም እጠረት ባለበት ሀገር ስራ ላይ መሰማራት አለመቻላቸው እንደሚያሳዝናቸው ገልፀዋል። የቲክቫህ አባላት እንዳሉት ከነሱ ብዙ ነገር ቤተሰቦቻቸው ቢጠብቁም እንኳን ለቤተሰቦቻቸው ሊሆኑ እራሳቸውን ችለው ከቤት መውጣት አልቻሉም። @tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
Mar 15, 2021