አዎን። በቁጥር 8፥ መምህርን፣ 9 ላይ አባት፣ 10 ላይ ሊቃውንት ብላችሁ እትጥሩ ይላል። ይህ ግን ለማለት የተፈለገው ግብዝነትን አትለማመዱ፥ እንዲሁም አታበረታቱ ለማለት ነው። ለምሳሌ:- ካህናት፣መምህራን፣ ፕሮፈሰር...or whatever ስለሆኑ ብቻ አክብሩኝ፣ ከፍ ያለ ቦታ አስቀምጡኝ የሚሉ ሰዎች ይኖራሉ። እናም እንደነሱ አትሁኑ፤ እንዳታበረቷቷቸው ለማለት ነው። እንጂ..ያስተማረህን፣ ሊያስተምርህ የሚችለውን መምህር አትበለው ለማለት አይደለም። እባትም ሲል.....ክርስቶስ የወለዳችሁን አባት አባት አትበሉ አይልም፣ የሱ ትዕዛዝ አይደለም። አባትን አባት አለማለት ደሞ ንቀት ነው። ግን እንድ ሰው አባት ልንል የሚገባው አባታችን (በስራውም አባት ለሆነው) ለሆኑት ነው። እነሱም ልጄ ብለው ይጠራሉ። (1&2ጢሞ 1፥4) (ቲቶ 1) (1ዮሐ 2፥1) ላይ ልጄ/ልጆቼ የሚለውን ቃል ይጠቀማሉ። ሐዋርያት ደሞ እንደሚታወቀው የክርስቶስን ፍቃድ እንጂ የራሳቸውን ቃል አይጠቀሙም። ሊቃውንት ማለት ሊቅ ከሚለው የወጣ ሲሆን ዐዋቂ፣ አለቃ፣ምሁር ማለት ነው። so, አንድም ሊቅ ሲባል ምሁር፤ ሊቃውንትም ማለት ምሁራን ማለት ነው። እናም ምሁራን የሚባሉት መምህራን እንደመሆናቸው እሱ ከላይኛው አንቀጽ የሚለይ መልስ የለም። ዋነኛው 'ሊቀ-' ብሎ የሚጀምረው ቅጥያ ግን "አለቃ" የሚለውን ይገልጻል። ሊቀ ሐዋርያት ጴጥሮስ ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሊቀ ዲያቆናት እስጢፋኖስ.....እያለ..እናም ይህ አለቅነታቸውን ወይም ሹም መሆናቸውን ለመግለጽ ነው።
Mar 11, 2021