ሰላም ሰላም ፡ ማራኪዬ ነኝ ። #5...✌ የዛሬው መወያያ ርዕሳችን የሚሆነው ስለ ሀገራችን ጉዳይ ይሆናል ። ለዚህ ጥያቄ መነሻ ሀሳብ የሆነኝ በቲቪ ላይ የሆነ ሰው ሲያወራ የሰማሁት ነገር ነው ። "እኛ ኢትዮጵያዊያን የውስጥ ችግሮቻችንን ቢለያዩንም ጠላት ከውጪ ሲመጣ ግን አንድ ነን ..." ነበር ያለው ። #1ኛ፦ የውጪ ጠላት ሲመጣ ሲመጣ ብቻ አንድ መሆን የሚል ነገር አዋጭ ነው ...❓ #2ኛ፦ የውጪ ጠላት ሲመጣ የሚመጣው አንድነት ለምን ሀገር ውስጥ ሌላ ጠላት ሳይመጣ እኛው እራሳችን ጋር አልሰራም ...❓ #3ኛ፦ ውስጣዊ አንድነትስ ሳይኖር ወደፊት ጠላትስ ቢመጣ አንድ ለመሆን ምን ያክልስ እርግጠኛ ነን ...❓ ፈጣሪ ፍጥረታትን ሁሉ ይባርክ ፡ አሜን ።
Mar 09, 20211,አይደለም ምክኒያቱም ውስጣዊ አንድነት የሌላት ሀገር በጊዜ ችግሩ መፍትሄ ካላገኘ የጊዜ ጉዳይ እንጂ መፍረሷ/መበታተኗ አይቀሬ ነው፡፡ 2,የሀሰት ትርክቶች/የታሪክ መዛባት በከፍተኛ ሁኔታ መኖሩና ህዝቡም አንድ ከሚያደርገው ነገር ይልቅ ልዩነቱ ላይ ብቻ ማተኮሩ፡፡ 3,ምንም መተማመኛ የለንም ማን ያውቃል በዚ ከቀጠልን ከሩዋንዳ የባሰ የዘር ፍጅት ሀገራችንም ሊያጋጥማት ይችላል፡፡
Mar 09, 2021