Esti drop some good የፉከራ ግጥሞች for assignment
Mar 09, 2021የሽለላና ፉከራ ግጥሞች ------------------------------ ✦ እህህ ነው እንጂ ያከሳው ደረቴን፣ ሳልበላ መች አደርኩ አንድ እንጀራ ራቴን። ✦ ከገደሉም አይቀር ይገድሏል ኤልሞሌ፣ ባለ ብዙ ጭፍራ ባለ ብዙ ሎሌ። ✦ እደጊ ጆሮዬ ነገ እቆርጥሻለሁ፣ ብዙ ብዙ ነገር ሰምቼብሻለሁ። ✦ ደመና ሲዳምን ይወረዛል ገደል፣ ወተት ይሸፍታል እንኳን ሰው ሲበደል። ✦ ሆሆ በለው ንቡን የሰፈረ እንደሆን፣ የተሠራው ሥራ እንዳይሆን እንዳይሆን። ✦ በድንጋይ ሲመታኝ መታሁት በኩበት፣ ምን ያደርግልኛል ያለጊዜው ጉልበት። ✦ ጠመንጃ ገዛለት ሀብታም ነው አባቱ፣ ልብ ሳይገዛለት አለቀበት ሀብቱ። ✦ ሐዘን በሳቅ ያልፋል ጊዜም በተረት፣ ጀግንነት ብቻ ነው አብሮ የሚሞት። ✦ ኮሶ ለታየው ሰው መድኃኒቱ ኮሶ፣ ማጠጣት ነው እንጂ መልሶ መላልሶ። ✦ እኛ መች አልንና የጎረቤት ጠጅ፣ እየበጠበጡ ይጠሩናል እንጂ። ✦ መረረኝ እንደ ሬት ፈጀኝ እንደ ሳማ፣ እንዲህ ያለ ነገር ጆሮዬ እየሰማ። ✦ ምን ያጣላችኋል በመሬት ጉዳይ፣ ዘሩ ያለቀ ለት ይቀር የለም ወይ። ✦ ያልበላኝን ሁሉ ሳክ ሳክ ኖሬ፣ በበላኝ ላይ ስደርስ አለቀብኝ ጥፍሬ። ✦ ወዲያ ማዶ ሆኖ ክፉ ሰው ይጣራል፣ ወዲህ ማዶ ሆኖ ክፉ ሰው ወይ አለው፣ ባናውቀው ነው እንጂ ይህ ነገር ለኛ ነው። ✦ ነገረኛ ውሃ እታች ቢቆሙበት እላይ ደፈረሰ፣ ጠላት መች ይተኛል ጥይት ካልቀመሰ። ✦ እኔን ከፋኝ እንጂ አገሬን መች ከፋው፣ አበቀለ ግራር ዝሆን የማይገፋው።
Mar 09, 2021