ሰላም የእመቤታችን ምሳሌዎች ከዘሁልቁ ጀምሮ የሚያወራ መፅሀፍ ካላቹ ወይም እናንተ የምታውቁ ከሆነ ላኩልኝ
Mar 07, 2021Ye Rodas tadese mestafoch
Mar 08, 2021ሰላም የእመቤታችን ምሳሌዎች ከዘሁልቁ ጀምሮ የሚያወራ መፅሀፍ ካላቹ ወይም እናንተ የምታውቁ ከሆነ ላኩልኝ
Mar 07, 2021Ye Rodas tadese mestafoch
Mar 08, 2021❤የሰው ልጅ ሕግን ተላልፎ በመበደሉ (ጥንተ አብሶ) ከእግዚአብሔርም ተለየ፡፡ በራሱ ትሩፋትም ወደ እግዚአብሔር መመለስና መዳን አልተቻለውም። ስለዚህ ድካሙን ያግዝለትና ድኅነቱን ይፈጽምለት ዘንድ ጌታ ለአዳም ቃል ኪዳን ገባለት። ቃል ኪዳኑም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በመስቀል ተሰቅዬ ሞቼ አድንሃለሁ የሚል ነበር። ለዚህ ቃል ኪዳን ፍጻሜም ምክንያት ትሆን ዘንድ እመቤታችንን በንጽሕና ፈጥሮ፣ ከጥንተ አብሶ ጠበቃት። በዘመነ ብሉይ የነበሩ ሁሉ በዚህ በደል የተያዙ ነበሩና (ሮሜ. 5፡12-14)። ነቢዩ ኢሳይያስ በተማጸነበት የትንቢቱ ክፍል ነው፡፡ ምዕራፉን ሲጀምርም “ሰማዮችን ቀድደህ ምነው ብትወርድ!” (ኢሳ. 64፡1) ብሏል፡፡ ይህን የተናገረ ኢሳይያስ በዘመነ ብሉይ ከነበሩ ሰዎች ሁሉ ለይቶ እመቤታችን ድንግል ማርያም በጥበበ እግዚአብሔር ከመጀመሪያው በደል (ጥንተ አብሶ) ተጠብቃ መቀመጧን በትንቢት መነጽር ተመልክቶ ነበር፡፡ ይህንንም ሲያስረዳ “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፣ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር” (ኢሳ. 1፡9) ብሏል፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞንም በመዝሙሩ “ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም” (መኃልይ. 4፡7) በማለት በምሳሌ የእመቤታችንን ፍጹም ንጽሕና ተናግሯል፡፡ እንደ ሰዶምና ገሞራ ሰዎች ጠፍተን፣ በኃጢአት ተይዘን እንዳንኖር የድኅነት ምክንያት የሆነች፣ ንጹሕ ዘር የተባለች፣ የባሕርያችን መመኪያ የሆነች እመቤታችንን ከአዳም ጀምሮ እስከ ኢያቄም አብራክ ያስቀረልን እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን፡፡ እርሷንም በቅድስናዋ መዓዛ ከርኵሰታችን ሽታ ታነጻን ዘንድ እንለምናታለን።
Mar 08, 2021mariam ko adis kidan lay new yalechw
Mar 08, 2021Yelem atifelg 😜😂 Misale sayhon erasuan ye Eyesus enatin be adis kidan wengel metsaft lay tagegnataleh😁😁
Mar 08, 2021ENE yefelekut msale newa
Mar 08, 2021