What's ur unforgettable childhood memory🖤
Mar 02, 2021እስቲ በልጅነቱ ሱቅ ተልኮ ፡ ግዛ የተባለውን የእቃ ስም እንዳይረሳ በአፉ ከራሱ ጋር እያወራ ሄዶ ልክ ሱቅ ሲደርስ ግዛ የተባለው ነገር የጠፋው ...?🙆 እኛ ቤት ብቻ ነው የhollywood ፊልም ሲታይ ልክ ፍቅረኛሞቹ ከንፈር ለከንፈር ሊሳሳሙ ሲሉ channel የሚቀየረው ...?🙆 እስቲ እንደኔ ፡ የአንደኛ ዓመት ልደቱ እሱን በሚበልጥ ትልቅዬ ድፎ ዳቦ የተከበረለት ...?🙆 እስቲ በልጅነቱ እንደኔ በእናቱ እጅ በቶፓዝ ምላጭ ፀጉሩን ተላጭቶ ፡ "መላጣ ፡ የስላሴ ጦጣ ፡ ሀምሳ ብሬን አምጣ" የተባለ ...?🙆 እስቲ የበዓል ሰሞን እቤታቸው ፍየል ተገዝቶ ፡ አንተ ልጅ ስለሆንክ ይጠፋብሀል አጠብቅም ተብሎ ፡ የዶሮ እግር ላይ ገመድ አስሮ ፡ ዶሮዋን የጠበቀ ...?🙆
Mar 03, 2021