ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ። በመጀመርያ በደስታም በሐዘንም ላላችሁ መልካም የአድዋ መታሰቢያ ቀን ይሁንላችሁ ማለት አፈልጋለው። እንግዲህ ውለን አድረን የማናየው የለምና ዛሬ ግራ ግብት እስከሚለኝ ድረስ የአድዋ በዓል መሆኑና የኮሎኔል ዐብይ ልደት መሆኑ አደናግሮኛል😂። ያውም ደሞ የመስቀል አደባባዩን ስናይ፤ ከሰዴን ሶዶው ፈርጥ፥ አባ ነፍሶ በተባለው ከጀነራል ባልቻ ሳፎ ጋር ፎቶው ሲለጠፍ አየው። ቆይ ግን ይህ ሰውዬ ወዴት እየሄደ ነው😂? ባይሆን ባይሆን ባልቻ ሳፎ፥ እምዬ/አዴ(ወ/ሮ) ሚኒልክን ከሞት አትርፎት ከዋሻው እንዳወጣው ሁሉ፤ እምዬ አብዮትን ከሞት ታድጎት ከቢሾፍቱ ያወጣውን የጀነራል ባጫ አባነፍሶ(ባጫ ደበሌ😂) ፎቶ መለጠፍ የነበረበት አይመስላችሁም?
Mar 02, 2021የምር እናውራ ከተባለ ይሄ ትውልድ (ከቀደዳ ባለፈ) የአድዋ ድል ምኑ ነው? መቼም በአንዲት አርቲስት ቂጥ ቀለም ሁለት ጎራ ለይቶ የሚፋለምን ሰው እንዴት በአድዋ ጎራ ትለያለህ ማለት ከባድ ነው። ይሁንና ከዓመት ዓመት የሚሳቡት የነገር ሰበዞች ቀጥነው ቀጥነው ወላ የአድዋ ጀግኖችን መከፋፈል ይዘናል። እሰይ የሚያስብል ነው ምጡቅነታች🙈🙈 'ከድሉ መሃል በእንዲህኛው ቀን በእንዲህኛው ሰዓት የተኮሰው የእኔ ብሄር ስለሆነ የዚህ ደቂቃ ድል የሚገባው ለእኔ ነው የሌላው ቀን ውጥንቅጥ ገደል ይግባ' 'ይህን ያህል ሬሳ ይገባኛል ምክንያቱም የዚን ያህል ነጫጭባ የገደለው የእኔ ብሄር ወታደር ነው' ዓይነት የታሪክ ክፍፍል የትምኮ አልታየም...🙆
Mar 02, 2021