Atse Minilik emeye minilik eyetebalu miterut lemndenew ? How did he got this nickname? Melkam ye del beal 🇪🇹🇪🇹
Feb 28, 2021አፄ ምኒልክ እንግዲህ እምዬ ምኒልክ እየተባሉ እንደሚጠሩ የታወቀ ነው። ይህን ስያሜ ያገኙትም እጅግ ሩህሩህ እና ለሰው አዛኝ መሆናቸው ነው። ይህን ከሚያረጋግጡልንም አብይ ምክንያቶች መካከል አንዱ ለአሽከሮቻቸው የነበራቸው አመለካከት ነው። ምኒልክ ከማይረሱት ልማዳቸው አንዱ ሠራዊታቸው ምግብ ሳይበላ እሳቸው አይበሉም ነበር። አንድ ጊዜ ከደጃች ውቤ ቤት ተጋብዘው ሄዱ። ደጃች ውቤም አማታቸውን ምኒልክን ከተቀበሉ በዋላ ወደ ቤት እንዲገቡ ቢጠይቋቸው "በፊት አሽከሮቼን አስገባና አብላልኝ።" ብለው እምቢ አሉ አሽከሮቹም ለግብር ሲገቡ የምኒልክንና የየመኳንንቱን በቅሎዎች የያዙ አሽከሮች ቀሩ። ይህን ያዩት ምኒልክ በቅሎአቸውን "ወዲህ አምጣት" ሲሉ አሽከሮቹ እየሮጡ በቅሎአቸውን አቀረቡላቸው። አብረዋቸው የነበሩት መኳንንት "ወዴት ሊሄዱ ነው?" እያሉ ሲጠይቁ ምኒልክ የበቅሎዋን መሳቢያ ለኮ ከአሽከራቸው ተቀብለው "ሂድና ምሳህን ብላ" አሉት። ሁሉም ደነገጡ ምንሊክም አሽከሮቻቸውን ተቆጥተው ወደ ግብር እንዲገቡ ሲያደርጉ እፊታቸው የነበሩት ፀሐፌ ትእዛዝ ገብረሥላሴ ከምኒልክ እጅ በቅሎዋን ለመቀበል "ይስጡኝ እኔ ልያዛት" አሏቸው። ምኒልክም "የኔን ተውልኝና ያንተን ካንተ አሽከር ተቀበል" አሏቸው። ከዚህ በዋላ መኳንንቱ ሁሉ ከአሽከሩ በቅሎውን እየተቀበሉ ሲይዙ አሽከር ምሳውን ሊበላ ወደ ግብር ገባ። ምኒልክም ከአንድ የኮክ ዛፍ ስር በቅሎአቸውን ይዘው ቆመው አሽከሮቻቸው በልተው እስኪወጡ ድረስ ጠጅ እየጠጡ ይጠብቁ ጀመር። AMEN lanchim melkam beale😊
Feb 28, 2021