Hey guys, 1 tyakie neberegie Orthodox negie tiktok layie memhir zebene emebetacin wedesemay argalecie silu semcie gragebtogial asredugie estie? Kalehywot yasemalgie amesegnalew🙏
Feb 25, 2021ያው ወደ ልጇ አረገች ነዋ በመላዕክት ተከባ
Feb 25, 2021Hey guys, 1 tyakie neberegie Orthodox negie tiktok layie memhir zebene emebetacin wedesemay argalecie silu semcie gragebtogial asredugie estie? Kalehywot yasemalgie amesegnalew🙏
Feb 25, 2021ያው ወደ ልጇ አረገች ነዋ በመላዕክት ተከባ
Feb 25, 2021Is it even a big deal mareg lemaryam?😊, hulun yefeterewn amlak be hodua teshekima yizalech eko❤️❤️❤️
Feb 25, 2021Siketl demo እርገት የመለኮት ባህርይ አይደለም መለኮት በሁሉ ምሉዕ ነው እርገት የፍጡር ባህርይ ነው በመፀሀፍ ቅዱስም ኤልያስና ቅዱሳን መላዕክት ሲያርጉ ተፅፉአል ማርያምም ቅድስት+የአምላክ እናት ናትና ወደ ልጇ አርጋለች።
Feb 27, 2021“እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘላለም ሞትን አያይም።” — ዮሐንስ 8፥51 sijemer kdusan aymotum esua demo chrash ye geta inat nat
Feb 27, 2021Of course argalech semayna mdrn yeyaze geta eyesus krstosn be mahtsenua yza mareg biansbat new inji aybezabatm...
Feb 27, 2021እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተነስታ ዐርጋለች ? ‹‹ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም››ከሚለው ቃል ጋር አይጋጭም ? በዓለም ዙሪያ ያሉ አብያተ ክርስቲያን በዚህ ዙሪያ ምን ይላሉ? መ/ር ታሪኩ አበራ #እባካችሁ ይህንን ትምህርት ለሰው ሁሉ ሼር በማድረግ ሰዎችን ከስህተት እንመልስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በልጇ ሥልጣንና አስነሽነት ከሞት መነሳቷና ማረጓ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በምሥራቅና ምዕራብ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ እንዲሁም በኦሬንትያል /አኅት አብያተ ክርስቲያን/ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ዓለም አቀፋዊ ትምህርት ነው። ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ሲወርድ በመጣው መንፈሳዊ ትውፊት መሠረትም በረካታ የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አባቶችና ጥልቅ እውቀትና መንፈሳዊ ቅድስና ያላቸው የነገረ መለኮት ሊቃውንት ተቀብለው የተስማሙበት የቤተክርስቲያን ታሪክ አካል ነው። አንዳንድ ወገኖች ለምን በመጽሐፍ ቅዱስ አልተጻፈም ብለው የድንግል ማርያምን ትንሣኤና ዕርገት ላለመቀበል ጉንጫ አልፋ ክርክር ቢያቀርቡም እርሷስ በልጇ ሥልጣንና አስነሽነት ተነስታ ዐርጋለች ።በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈልን ሕይወት የሚሆነንና ለድኅነታችን ወሳኝ ትምህርት የሆነው የክርስቶስ ልደት፣ጥምቀት፣ስቅለት፣ ትንሳኤና ዕርገት ነው እንጂ የእመቤታችንም ሆነ የሌሎች ቅዱሳን ሁሉ ታሪክ ይጻፍ ቢባል ዓለም በሙሉ ባልበቃ ነበር።አንድ ነገር አልተጻፈም ማለት አልተደረገም ማለት አይደለም።እንኳን የእመቤታችን ታሪክ ይቅርና ጌታ ያደረገው ታሪክ በሙሉ እንዳልተጻፈ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ እንዲህ ሲል በግልጽ ይመሰክራል (የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 20) ---------- 30፤ ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤ 31፤ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።" ዛሬ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የድንግል ማርያምን ትንሳኤ አጥብቀው ቢቃወሙም የፕሮቴስታንት እምነት መስራች የሆነው ማርቲን ሉተር ግን ድንግል ማርያም በክብር መነሳቷንና በመንግስተ ሰማያት በክብር እንዳለች እንዲህ ሲል በግልጽ አስቀምጧል፦ "There is no doubt that the virgin Mary is in heaven.How it happened we do not know " (Martin Luther's Works, Vol 10) "ድንግል ማርያም በመንግስተ ሰማያት እንደሆነች ጥርጥር የለውም።እንዴት ሆኖ እንደሆነ ግን አናውቅም።" ብሏል ለእርሱ የረቀቀውን የትንሳኤና የዕርገቷን ነገር መንፈስ ቅዱስ ሃይማኖታቸው ለቀና አባቶች በስፋት ገልጾላቸው ጽፈውልን አልፈዋል። የእመቤታችን የልደትና የአስተዳደግ ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባይጻፍም በሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ ሁሉ ትንሳኤና ዕርገቷም በሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍት በስፋት ተጽፏል።ለዚህም ነው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ታሪክ ሆኖ የእመቤታችን ትንሳኤና የዕርገት መታሰቢያ በዓለም ዙሪያ ሁሉ በክብር የሚታሰበው። አንዳንድ መሪጌታነን፣የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች ነበርን ፣ የቤተክርስቲያን መጻሕፍትን እናውቃለን የሚሉ፤ ነገር ግን በጥራዝ ነጠቅ እውቀት የታጀሉ ሰዎች ስለ እመቤታችን ልደት፣ቤተ መቅደስ ስለመግባቷ፣ዜና እረፍቷንና ትንሣኤዋን የሚገልጸውን ታሪክ ሁሉ የኢትዮጵያውያን ድርሰት ነው፣ይህ ታሪክ አልተደረገም። በማለት ያሳደገቻቸውን ቤተክርስቲያንን በመንቀፍ የአዕምሯቸውን ጥበትና የዕውቀት አድማሳቸውን ውስንነት በአደባባይ ሲገልጡ እያየን ነው። ይህ ለማይረባ አዕምሮ ተላልፎ መሰጠታቸውን ማሳያ ነውና መንፈስ ቅዱስ ልባቸውን እንዲፈውሰው ጸሎታችን ነው። ጥንታውያን አባቶቻችን በቅድስና የተዋቡ፣ንጽሕናን ገንዘብ ያደረጉ፣በክርስቶስ ፍቅር ልባቸው የተሰበረና ዓለምን ንቀው የመነኑ ስለነበሩ መንፈስ ቅዱስ የረቀቀውን አጉልቶ የራቀ ውን አቅርቦ ብዙ ምሥጢራትን ገልጾላቸው ይህችን ታሪካዊትና ሐዋርያዊት የሆነች ታላቅ ቤተክርስትያን ከነሙሉ ክብሯ አስረክበውን አልፈዋል።ዛሬ ለሥጋ በሚመች ዝርክርክ ኑሮ እየኖርንና ከሌሎች ቤተ እምነቶች ደካማ ዶክትሪን እየቀላወጥን ቤተክርስትያንንና አበውን ለመንቀፍ መነሳት እጅግ ኋላቀርነት ነው። # ‹‹ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም››ዮሐ 3፡13 የሚለው ቃል ምሥጢሩ ምንድን ነው? አንዳንዶች ይህንን ጥቅስ ያለ ቦታው በመጥቀስ የእመቤታችንን ትንሳኤና ዕርገት ለመንቀፍ ሲወራጩ እናያለን ። ሊቃውንት አባቶች እንዳስተማሩት ግን ይህ የጌታችን ቃል የሚከተሉትን አምስት ነጥቦች ያስረዳል፡፡ 1. ከጌታችን በቀር ከሰማያዊ ዙፋን የወረደ የለም፡፡ ሰማይ የልዕልና ስፍራ፣ የእግዚአብሔር ዙፋን ነው፡፡ በዚያ ዙፋን የተቀመጠ፣ ሰውንም ለማዳን ከዙፋኑ የወረደ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ሌላ በዚያ ዙፋን የተቀመጠ ከዚያ ዙፋንም የወረደ የለም፡፡ ሰውን ለማዳን ከዙፋኑ የወረደው በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው፡፡ 2. ከጌታችን በቀር በራሱ ፈቃድ ከሰማይ የወረደ የለም፡፡ ፍጡራን (መላእክትና ሰዎች) ወደ ሰማይ ቢወጡም ቢወርዱም በራሳቸው ፈቃድ አይደለም፡፡ በራሱ ፈቃድ በአባቱ ፈቃድ ከሰማይ የወረደ ወደ ሰማይም የወጣ እርሱ ብቻ ነው፡፡ በራሱ ፈቃድ ከሰማይ የወረደው በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው፡፡ 3. ከጌታችን በቀር በባህርይው መለወጥ የሌለበት፣ አንድ ባህርይ የሆነ፣ ይህንንም በራሱ ፈቃድ የወሰነ የለም፡፡ ከሰማይ የወረደው ወደ ሰማይ የወጣውም አንድ አካል አንድ ባህርይ ነው፡፡ ከሰማይ አንድ አካል አንድ ባህርይ ሆኖ ወርዶ፡ ሁለት ባህርይ ሁለት አካል ሆኖ ወደ ሰማይ የወጣ አይደለም፡፡ ልክ አንድ አካል አንድ ባህርይ ሆኖ እንደወረደ አንድ አካል አንድ ባህርይ ሆኖ ወጣ ማለት ነው፡፡ አንድ ባህርይ ሆኖ ወርዶ አንድ ባህርይ ሆኖ ወደ ሰማይ የወጣው በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው፡፡ 4. ፍጹም ሰው፣ ፍጹም የባህርይ አምላክ ከሆነ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሰማያዊ እውቀት የባህርዩ የሆነ፡ ሰማያዊ ሀብትን ሰማያዊ እውቀትን ገንዘብ ያደረገ ምድራዊ መምህር የለም፡፡ ሰማያዊ ሀብትን ሰማያዊ እውቀትን ገንዘብ ያደረገ ከሰማይ የወረደው ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ከምድራዊያን መምህራን በራሱ ወደ ሰማይ ወጥቶ፡ ተመልሶ ወርዶ ያየውን የሚያስተምር የለም፡፡ እርሱ ከሰማይ የመጣው ግን ሰማያዊ ምስጢርን ለማስተማር (ለመግለጥ) የራሱ ባህርይ (የባህርዩ) ነው፡፡ 5. ከጌታችን በቀር በኅልውና ያየውን የሚገልጥ፡ በሰማይ ሆኖ በህልውና ያየውን በህልውና የሰማውን መጥቶ የሚያስተምር ምድራዊ መምህር የለም፡፡ በሰማይ ሆኖ በህልውና ያየውን በህልውና የሰማውን የራሱን ምሥጢር ያስተማረ እርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው፡፡ ለመሆኑ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ድንግል ማርያም አልተነሳችም የሚሉት መሞቷን ከየት አገኙት? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደሆነ ፈጽሞ አልተጻፈም።የድንግል ማርያም ልደትም ሆነ ዜና እረፍት በሌሎች መጻሕፍት መነገሩን ከተቀበልን ትንሣኤና ዕርገቷን አልቀበልም ማለት አዕምሮን ማጥበብ ነው።ደግሞም አንድ እውነትን ለማወቅ ለአቅመ መረዳት መድረስ ያስፈልጋል ።በጥራዝ ነጠቅ እውቀትና ቅድስና በጎደለው የተዝረከረከ ሕይወት እየኖርን በቅድስና ለእግዚአብሔር የታመኑ፣ በአዕምሮ እጅግ የበሰሉና በእውቀት የመጠቁ ሊቃ
Feb 25, 2021lek ende lijewa aregalech wed semayy
Feb 25, 2021