ጭውውት አቅርቡ ተብለናል እና 6 ሰው ሊያሳትፍ የሚችል አጠር ያለ ልቦለድ ውስጥ ያለ ጭውውት ንገሩኝ (መፅሀፉን ጠቁሙኝ)
Feb 21, 2021May be የ ከንቲባው ልጅ
Feb 22, 2021ጭውውት አቅርቡ ተብለናል እና 6 ሰው ሊያሳትፍ የሚችል አጠር ያለ ልቦለድ ውስጥ ያለ ጭውውት ንገሩኝ (መፅሀፉን ጠቁሙኝ)
Feb 21, 2021May be የ ከንቲባው ልጅ
Feb 22, 2021Grade 6 txt book *gib nech*
Feb 22, 2021📚አጭር ልቦለድ 📖 👨 አደራው 👧 ክፍል #1 💇♂ ጸጉሬን እየተቆረጥኩ ነው - “ታምሩ የወንዶች ባርበሪ”። ፀጉር አስተካካዩ ወሬ ይዟል፤ ሙግት ብለው ይሻላል፤ ቤቱን ካከራዩት ሠው ጋር። እኔ ግን ትዕግስቴ እየተሟጠጠ ነው። “አረ እባክህ ቶሎ በልልኝ፤ እዚህ ዋልኩ እኮ” አልኩ በብስጭት። መልስ አልሠጠኝም፤ ሙግቱን ቀጥሏል። “ስማ ታምሩ፤ ነግሬሃለሁ። 2000 ብር ከበደኝ ካልክ፣ እቃህን ጠቅልለህ ውጣ!” አሉ አከራዩ። ታምሩ፣ በቶንዶስ በቀኝ በኩል ፀጉሬን ለማስተካከል ዞሯል፤ የግራውን ሳይጨርስ። ቀልቡ ስራው ላይ አይደለም፤ እያየም አይመስለኝም የሚቆርጠኝ። ይባስ ብሎ ቶንዶሱን አስቀምጦ አከራዩ ላይ አፈጠጠ። “ለዚህ ኩሽና 2000 አልከፍልም። እወጣልዎታለሁ። ይብላኝ ለርሶ እንጂ፣ ደንበኞቼ የሄድኩበት ይከተሉኛል”:: “ጥሩ፤ ዛሬውኑ ውጣልኝ” ። “ሠውዬ፣ እኔን መጀመሪያ አስተካክለህ ጨርስና ትወጣለህ” አልኩ - ቢቸግረኝ። ሞባይሌ ይጮሀል፤ ከቅድም ጀምሮ። አላነሳሁትም፤ ባለቤቴ ነች። ዛሬ ጠዋት ተጣልተን ነው የተለያየነው። መጣላት ሳይሆን ትንሽ ግጭት ብጤ። ዛሬ ቢሾፍቱ ለስራ ሄዳለች። አዳሯን ነው የሄደችው። መሄድዋ አደለም ያናደደኝ። በጠዋት፣ ጎረቤታችን ወ/ሮ አማከለች ጋ ሄዳ፣ እሷ ስለማትኖር ልጃችን ከትምህርት ቤት ስትለቀቅ እንዲያመጥዋት አደራ ስትላቸው አበገነችኝ። እኔ አባትዋ እያለሁ፤ ባዳ መለመን? እኔ አልችልም አላልኳትም። በዚህ ተናድጄ ነው በጠዋት አምቧጓሮ የፈጠርኩት። “አይ ያንተ ነገር። አንዴ አልተመቸኝም፤ አንዴ ረሳሁት ብለህ እንዳትቀርባት ብዬ ነው” ስትለኝ የበለጠ ቱግ አልኩ። ረሳሁት ብለህ?... እንዴት ነው ልጄን የምረሳው! ደግሞስ፣ ስራ የት አለና ነው፣ ልጄን ከት/ቤት ለማምጣት ጊዜ ያጣሁትና ያልተመቸኝ። ደላላ ሁሉ በየካፌው ድዳችንን አስጥተን አደል እንዴ የምንውለው። ይሄን ደግሞ ጠንቅቃ ታውቃለች። በተለይ፤ በሚጡ ጉዳይ ለአደራ አትበቃም ብላ እንደ ዘበት መናገር ልማድዋ ነው። ይሄ በጣም ያናድደኛል። ባለፉት ስድስት ወራት ደግሞ፣ በጣም ብሶባታል። ምንም እድል አትሰጠኝም። መቆጣቴን አይታ መለስ አለች። “እሺ፤ እኔማ እንደ ሌሌሎቹ ልጆች፣ አባትዋ ቢያመጣት ደስ ይለኛል” ስትል፣ ተቃጠልኩ። እኔ ከሌሎች አባቶች አንሳለሁ? “ብቻ፣ አደራህን ዘጠኝ ሰዓት ከት/ቤት ስለምትለቀቅ ፤ እሩብ ጉዳይ ድረስላት። ብቻዋን እንዳትቀር አደራ!!!” ያደራው ብዛት! ልጄን ከት/ቤት አምጥቺያት አላውቅም። እንዴት አድርጌ? እድሉ መች ተሰጥቶኝ። ሚጡ፣ ዛሬ ከት/ቤት የማመጣት እኔ እንደሆንኩ ስትሰማ፣ በደስታ ፈነደቀች - “ባቢ ጓደኞቼ አባት የለሽም እያሉ ይተርቡኛል። ዛሬ አሳያቸዋለሁ፤ ታድዬ”። ወይኔ ልጄ! ሳልሞት በቁሜ። ንዴቴን ለመወጣት፣ ወ/ሮ አማከለች ቤት ሄጄ፤ “ተውት ግድየለም ልጄን እኔ አመጣታለሁ” አልኳቸው ኮስተር ብዬ። “እርግጠኛ ነህ? እኔ እኮ ምንም ስራ የለኝም። ተጎልቼ ነው የምውለው” ብለው መለሱልኝ። ©ከወደዱት ክፍል #2 ይቀጥላል ። Join us... ✦✺ @Minteno ✺✦ ✦✺ @Minteno ✺✦
Feb 22, 2021