ሰላም ሰዎች ሰምታችሁ ያስገረማችው ታሪካዊ ክስተት ወይም መጣጥፎች እና አስቂኝ ነገሮች እንዲሁም የድሮ የጋዜጣ እትም መግለጫዎች በአጠቃላይ ብታጋሩ እባካችሁ :: አመሠግናለሁ
Feb 14, 2021ሰላም ሰዎች ሰምታችሁ ያስገረማችው ታሪካዊ ክስተት ወይም መጣጥፎች እና አስቂኝ ነገሮች እንዲሁም የድሮ የጋዜጣ እትም መግለጫዎች በአጠቃላይ ብታጋሩ እባካችሁ :: አመሠግናለሁ
Feb 14, 2021Legend 🥇
Feb 14, 2021ባለ ብዙ ሚስቶች ኢትዮጵያዊ ንጉሥ ----------------------- በርካታ ሚስቶች በይፋ በማግባት ተወዳዳሪ ያልተገኘላቸው (ሪኮርድ) የሰበሩ ኢትዮጵያዊ ንጉሥ ልጅ ኢያሱ መሆናቸው ይነገራል። ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ "የታሪክ ትዝታዬ በአቤቶ ኢያሱ ዘመን" በሚለው ያልታተመ ጽሑፋቸው ውስጥ ንጉሥ (ልጅ) ኢያሱን እንዲህ በማለት ይገልጹዋቸዋል። "መልካቸው ቀይ፣ ቁመታቸው ሎጋ ድልድል፣ ዓይናቸው ጉልህ ነው። ጠጉራቸው ዞማ ነው፣ ሻሽ አንዳንድ ጊዜ በራሳቸው ላይ ያደርጋሉ። በጠባይ በኩል ግልጽ ናቸው፣ ነገረ ሰሪን አይወዱም፣ የጉብዝና ወሬ ያስደስታቸዋል፣ ፈረስ መጋለብ ይወዳሉ።" ንጉሥ ኢያሱ ከሚታወቁባቸው ባህርያት አንዱ በሄዱበት ሁሉ ሚስት ማግባታቸው ነበር። ብላታ መርስዔ ኀዘን የንጉሥ ኢያሱ ሚስቶች ነበሩ ብለው የዘረዘሩዋቸው የሚከተሉት ናቸው፦ 1. ወይዘሮ አስቴር መንገሻ 2. ወይዘሮ ሰብለወርቅ ኃይሉ 3. የአባ ጅፋር ልጅ 4. ወይዘሮ አስካለ ጆቴ (የደጃዝማች ጆቴ ልጅ) 5. የደጃዝማች አቡበከር ጨኖ ልጅ 6. ወይዘሮ ትሰሚ አንዳርጌ 7. ከአፋር የመንቶች ዘር 8. ከጥሙጋ የነሳሊህን ዘር 9. ወይዘሮ ዳሽን (የደጃዝማች ኩምሳ ልጅ) 10. ወይዘሮ ጥሩወርቅ አበጋዝ (ከየጁ ወረሼህ ተወላጅ) ከነዚህም ጋር ብዙ ዕቁባቶች ነበሩ። 📚 #ከታሪክ_ማህደር 📖 Join us... ✦✺ @Minteno ✺✦ ✦✺ @Minteno ✺✦
Feb 14, 2021