Hey guys, me and my friends got into an argument and we wanted to settle this, the topic is We know that if a couple wants to get married by Teklil they have to be virgins ena does mastubation count as losing virginity for the man???
Feb 07, 2021Gibre awnan Yibalal they should repent To their father and give them the right picture of what you did it really depends ግብረ አውናን ኃጢአት መሆኑ እሙን ነው። ሆኖም ግን ከሥርዓተ ተክሊል ጋር የሚገናኝ አይደለም። ጉዳዩ በእርግጥ ጥንቅቅ ያለ ቀኖና የወጣለት ስላልሆነ፥ ብዙ ጊዜ አባቶች የንስሃ ልጃቸውን ሁኔታ አይተው ውሳኔ የሚሰጡበት ነው። በጉዳዩ ላይ ጠበቅ ያለ ምልከታ ያላቸው ሲከለክሉ፥ ብዙዎች ደግሞ አይከለክሉም። ሃይማኖታዊ መጽሐፍትን መሠረት በማድረግ ግን፥ ሴቷም ሆነች ወንዱ ግንኙነት ካልፈጸሙ በስተቀር ተክሊል አይከለከሉም።አንዳንድ ሰዎች ማስተርቤሽን ሲፈጽሙ ከኖሩ በኋላ የንስሐ አባቴ ፈቅደውልኛል በማለት ተክሊል ለመፈጸም ሲዳፈሩ ይታያል። እነዚህ ሰዎች ሰለ ማስተርቤሽን በጥልቀት ለንስሐ አባታቸው ሳይናገሩ በሥጋ ብቻ ድንግል መሆናቸውን አጉልተው በማምታታት / በማድበስበስ/ ኑዛዜ ፈጽመው ወደ ተክሊል ለመምጣት የሚያደርጉት ጥረት ለመአት ካልሆነ የበረከት መንገድ አለመሆኑ ግልጽ ጉዳይ ነውና መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ተወዳጆች ከድፍረት የሚገኝ ምንም አይነት መንፈሳዊ በረከት የለም። ድፍረት መንፈሳዊ ኪሳራን ያስከትላል ለዚህ ነው ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ያለው " የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያህን ጠብቅ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ።" (መዝሙረ ዳዊት 19: 13) ምን አልባት አንዳንድ ካህናት ሰለዚህ አይነት ኃጢአት ግንዛቤ ሳይኖራቸው ቀርቶ ተክሊል ፍጽሚ ተክሊል ፈጽም ቢሉን እንኳን ራሳችንን ዝቅ በማድረግ አይገባኝም ልንል ያስፈልጋል።
Feb 07, 2021