Himem yazele fkir yemilew liboled eskemechereshaw yalew kale lakulign please
Feb 04, 2021Send the channel enji dude
Feb 05, 2021Himem yazele fkir yemilew liboled eskemechereshaw yalew kale lakulign please
Feb 04, 2021Send the channel enji dude
Feb 05, 2021#ህመም_ያዘለ_ፍቅርን ፡ ፡ #ምእራፍ_ሁለት ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ #በክፍለማርያም ፀሀይዋ ለመጥለቅ ጥቂት ሰዐታት ይቀራታል እስዋን እየተመለከቱ ብዛት ያላቸዉ ወንዶች ግቢዉ ዉስጥ ከወዲህ ወድያ ይንጎማለላሉ። ፍፁም በብቸኝነት ተቆራምቶ ከተቀመጠበት ጥግ ተነስቶ ቆመና ወደ ሰፊዉ ክፍል አምርቶ ወረቀት እና እስኪርቢቶ አንስቶ መፃፍ ጀመረ። ለመጀመርያ ጊዜ ቤዛዊትን ያገኛት ቀን ሰአት ጠይቃዉ ስትሰድበዉ ታሪኩን እየፃፈ ከታሰረ ለመጀመርያ ጊዜ ፊቱ ላይ ፈገግታ ተነበበ መፃፉን አላቋረጠም የሚያስታዉሳቸዉን የእሱን እና የቤዛዊትን ታሪክ ወረቀቱ ላይ እየከተበዉ ነዉ። ትምህርት ቤት ዉስጥ የጠቀሰችዉን ሲያስታዉስ ድምፅ አዉጥቶ መንከትከት ጀመረ ከጎኑ የነበሩት እስረኞች እየገላመጡት ከአጠገቡ ተነስተዉ እራቁት ማንም ሰዉ ያንተን ህመም እንዳንተ አያመዉም ማንም ሰዉ አንተ ያሳለፍከዉ ከባድ ነገር ለእሱ ክብደቱ አይታወቀዉም መሸከም ስትችል ተቋቁመሀዉ ስታልፍ ያበረታሀል እንጂ አቅቶህ ስትወድቅ የሚያነሳህ ውስን ነዉ። መፃፉን እየቀጠለ ነዉ ቤዛዊት ፅፋ የምትሰጠዉን ወረቀቶች አሁንም ድረስ ያስታዉሳቸዋል ህመሟን እብደቷን ሳያዉቅ ቀሚስሽ አጥሯል ሲላት ጠልፎ የሚጥል እረጅም ቀሚስ ለብሳ ቤቱ የመጣችዉንም አልረሳዉም አሁንም እንደታመመች አዉቆ ስላልተዋት ስላልራቃት በራሱ ደስተኛ ነዉ። ቤዛዊትን ሲያስብ ፈገግታዋ የፊቷ እንቅስቃሴ አይኑ ላይ ይታየዋል ሳቋ በጆሮወቹ ዛሬም ያስተጋባሉ ንዴትዋን ኩርፊያዋን ህመሟን ሲያስብ ብታናድደዉም ስለተላመዳቸዉ እንደ እንከኖቿም አይቆጥርባትም የእሱን በድንገት በአጋጣሚ ፍቃዱ የሚባልን የተረገመን ፍጥረት በንዴት ተገፋፍቶ መግደሉን ሲያስብ ፀፀት መላ ሰዉነቱን እየወረረዉ የጀመረዉን ፅሁፍ አቁዋርጦ ማልቀስ ጀመረ። ፍፁም እስር አልተመቸዉም ለነገሩ መታሰር ለማን ይመቻል ገና አሁን ወዳለበት የእስር ግቢ እንደገባ የሬሽን መዝገብ ዉስጥ ስሙ ስላልተካተተ ደረቅ ዳቦ ብቻ ቀምሶ ትራስ እያስፈለገዉ ፍራሽ ላይ ጋደም አለ ለማሰብ ግዜ አላገኘም እራሱን ሀይለኛ ህመም እየተሰማዉ ነዉ። ሰዉነቱ በትኩሳት ግሎ ነገር ግን ብርድብርድ እያለዉ እየተንቀጠቀጠ ለሊቱን እንቅልፍ በአይኑ ሳይዞር ነጋ የመከራ ለሊት ይረዝማል ከታሰረ ሳምንት ወራት የቆየ ይመስለዋል ጠዋት ለህክምና የእስር ቤቱ ግቢ ካለዉ ክሊኒክ ለመሄድ ቢሞክርም ወረፋ ስላለ እንዲታገስ ስለተነገረዉ መራመድ እያቃተዉ በልቡ "መሞቴ ነዉ" እያለ እንደምንም ፍራሹ ላይ ወድቆ ለመተኛት ሞከረ። ቤዛዊት አይምሮዋ እየተረጋጋ ሲመጣ እማማ ስንቅነሽን ለፍፁም ምግብ እንዲቋጥሩለት አርጋ በተዘበራረቀ ስሜት ዉስጥ ሆና እንባ እየተናነቃት ወደ ፍፁም አመራች እስካሁን ፍፁም ፍቃዱን መግደሉን አላመነችም "የማይሆን የማይታሰብ ነገር" ትላለች ከአፏ እያመለጣት ስትራመድ የእስር ቤቱ ግቢ መግቢያ ስትደርስ የልብ ምቷ መፍጠን ጀመረ ፍፁምን ካየችዉ ቆይታለች በፖሊሶች ታጅቦ ሲያልፍ ካየችዉ ወድያ ምንም የምታስታዉሰዉ ነገር አልነበረም እድሜ ለእማማ ስንቅነሽ እና ለልጃቸዉ ለጌታቸዉ ስታስቸግር ስትረብሽ ተንከባክበዉ ለዛሬ እንድትበቃ ላገዟት ዉስጥ ገብታ የምትፈልገዉን ሰዉ ስም ተናግራ ቆማ መጠበቅ ጀመረች። ፍፁም አይኖቹ ቀልተዉ ደም መስለዋል በተኛበት ፍራሽ እንደሰመመን "ፍፁም ደምሴ" እየተባለ ሲጠራ ይሰማዋል መነሳት ግን አልቻለም በሞት እና በህይወት መሀል ያለ እየመሰለዉ ሲያጣጥር ቆይቶ የቤዛዊት ምስል ፊቱ ላይ ድቅን ስላለበት አይኖቹ እንባ አዝለዉ እንደምንም ተነስቶ ለመቀመጥ ሞከረ "ፍፁም ደምሴ ጠያቂ መጥቶሎታል" የሚል ድምፅ ስለሰማ እያቃሰተ ወደ ዘመድ ጥየቃዉ ቦታዉ ለመሄድ መታገል ጀመረ። ቤዛዊት እንደሆነች አስቀድሞ ልቡ አዉቆታል ጥቂት እንደተራመደ ግን የማጥወልወል ስሜት ስለተሰማዉ ለመረጋጋት አስቦ ለመቆም ሲሞክር ወደቀ ጨለማ እየታየዉ የነበረ ቢሆንም ቀስበቀስ ጨለማዉም ጠፍቶ እራሱን ስቶ ወድቆ ቀረ። 💫ይቀጥላል💫 ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
Feb 05, 2021